የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር | ጤና እና አካባቢ | DW | 15.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር

በተለያዩ ምክንያቶች ከአፍንጫ ደም ሊፈስ ይችላል። ነስርየምንለዉ ማለት ነዉ። ብዙዎች መንስኤዉ ምንድነዉ ብለዉ ይጨነቃሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:39
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:39 ደቂቃ

ነስር

ነስር ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የመሆኑን ያህል አብዛኛዉን ጊዜ ቤት ዉስጥ ሊቆጣጠሩት የሚቻል እንደሆነ አንዳንድ የህክምና ጽሑፎች ይጠቁማሉ። ሆኖም አልፎ አልፎ ደግሞ ብዙ ደም የሚፈስበት ከባድ ነስር ሲያጋጥም የሀኪም ርዳታ ማግኘት አማራጭ እንደማይኖረዉም ያሳስባሉ። የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር መንስኤዉ አንድ ብቻ አይደለም፤ የተለያዩ ህመሞች እና ምክንያቶች ሊያመጡት እንደሚችሉ ዶክተር ቶሌራ ወልደየስ የዉስጥ ደዌ ከፍተኛ ሃኪም አስረድተዋል።

Nasenbluten

ሲነስር ጎንበስ ብሎ አፍንጫን ቆንጥጦ መያዝ

መንስኤዎቹ የሚጣሩት ችግሩ ያጋጠመዉ ግለሰብ ሃኪም ጋር ቀርቦ በሚደረግ ምርመራ እና ማብራሪያ አማካኝነት ነዉ። እንደሃኪሙ ከሆነ ነስሩ ከፍተኛ ሲሆን ብቻ አይደለም ወደሃኪም መሄድ የሚገባዉ። የሚነስረዉ ሰዉ መንስኤዉን ለማወቅ ከአንገት በላይ ህክምና ባለሙያ ዘንድ ሄዶ በምን ምክንያት ያ እንደተከሰተ መመርመር ይኖርበታል። ነስር በሽታ ነዉ? አንድ ሰዉ ሲነስረዉ በመጀመሪያስ ምን ማድረግ ይኖርበታል? የሃኪሙን ማብራሪያ እና ምክር ለመከታተል የድምጽ ዘገባዉን ይጫኑ።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic