የአፍሪካ ህብረት ስብሰባና የአልበሽር ክስ | ኢትዮጵያ | DW | 26.07.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአፍሪካ ህብረት ስብሰባና የአልበሽር ክስ

በኡጋንዳ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ የአልበሽር ክስ መሪዎቹን ለሁለት ከፍሏል። የአፍሪካ ህብረት ዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአዲስ አበባ ሊከፍት ያቀደውን ጽህፈት ቤት ለጊዜው አልተቀበለውም።

default

የአልበሽር ክስና የአፍሪካ መሪዎች

ኡጋንዳ የተሰበሰቡት የአፍሪካ መሪዎች አጀንዳቸው የእናቶችን ጤና የተመለከተ ነበር። ከሁለት ሳምንት በፊት በካምፓላ የደረሰው የቦምብ ጥቃት የስብሰባውን ትኩረቱን ቀይሮታል። በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚፈለጉትን የሱዳኑ መሪን በተመለከተ የመሪዎቹ ስብሰባ ለሁለት ተከፍሎ ተካሂዷል። ኡጋንዳ የዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት አባል ሀገር በመሆኗ አልበሽር ወደስብሰባው አልሄዱም። ምንም እንኳን የህብረቱ የወቅቱ ፕሬዝዳንት የማላዊ መሪ ቢንጉ ዋ ሙታሪካ የአልበሽር ክስ ተቀባይነት የሌለው ነው ቢሉም ኡጋንዳ ላይ የተሰበሰቡት መሪዎች ግን ለሁለት ተከፍለው ተከራክረዋል። እንደ ደቡብ አፍሪካ፤ ጋናና ቦትስዋና ያሉ ሀገራት ከዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ጎን ሲቆሙ ግብጽና ሊቢያ ተቃውመውታል። ዶክተር ዳዲሞስ ሃይሌ በዓለም ዓቀፍ ድንበር የለሽ ጠበቆች ቡድን የዓለም ዓቀፍ ህግ ፕሮግራም ክፍል ሃላፊ የመሪዎቹን ለሁለት መከፈል ዲሞክራት ሀገር ከመሆን ካለመሆን ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ይገልጻሉ።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic