እንደ አንጎላ ያሉ አንዳንድ የነዳጅ ዘይት አምራች አገራት፣ የዓመት የእድገት መጠናቸዉን ከ20 በመቶ በላይ ሲያደርሱ፤ ሌሎች ሀገራት ደግሞ ማዕድንም ሆነ የነዳጅ ዘይትን ማዉጣት የጀመሩት ከቅርብ ግዜ ወዲህ ነዉ። የፖርቱጋል ቋንቋ ተናጋሪዋ ሞዛንቢክ ለምሳሌ በዓለማችን በከፍተኛ ደረጃ ከሰልን እና ጋዝን ለማምረት ጥሩ ጅማሮ ላይ ናት። የዓለማችን ኢኮነሚ በጥሪ ሃብት እጥረት ሲጨናቅ- የአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገቷ በመፋጠን ላይ ይገኛል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የአፍሪቃ ጥሪ ሃብት ምርት መጠናከር፤ በዓለም የገበያ ዋጋ ላይ እና በአቅርቦት ፍላጎት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ፤ የአህጉሪቱ ኢኮነሚ ላይ ተፅኖ ሊያሳድር ይችላል። በሌላ በኩል ጥሪ ሃብቱን በማከፋፈሉ ረገድ የከባቢ አየር መበከል፣ ሙስና እና ግጭቶች አዲስ በተጠናከረዉ ምጣኔ ሃብት ላይ ጉዳትን ያስከትላሉ። "በቂ የጥሪ ሃብት" በከርሰ ምድራቸዉ መገኘቱ እድገትን ሊያስገኝላቸዉ ሲገባ፤ ችግርን ይዞባቸዉ መጥቶ ይሆን? ይዚህ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለ ኢኮነሚ፤ ለአፍሪቃ ሀገራት እና ህዝቦችዋ የሚያመጣላቸዉ ጥቅም ምን ይሆን? የዶቼ ቬለ ዘጋቢዎች መልስ ያፈላልጋሉ።