የአፍሪቃ የአዳዲስ ግኝቶች ነክ ጉባዔ፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 05.02.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የአፍሪቃ የአዳዲስ ግኝቶች ነክ ጉባዔ፣

የሰው ብቻ ሳይሆን የሥልጣኔውም ጭምር መገኛ የሆነው ግዙፉ የአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ለብዙ ምዕተ ዓመታት ተዳክሞና በሌሎችም ተጽእኖ ሥር ከቆየ በኋላ ተመልሶ በዘመናዊ ሥልጣኔ ለማገገምና ርምጃ ለማሳየት የውጭ የሥነ ቴክሊክ ዝውውር ፣ አንዱ መንገድ ቢሆንም

በዋናነት፤ በአፍሪቃውያን ተመራማሪዎች ጥረት የራሱን ዕድገት ራሱ መምራት እንደሚበጀው ግንዛቤ ከተጨበጠ ቆይቷል። በመሆኑም የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ መሥፋፋት የልዩ ሎልዩ ፈጠራ ውጤቶች(ግኝቶች)፣ ለክፍለ ዓለሙ ሁለንተናዊ ጥንካሬ ተፈላጊዎች መሆናቸው በጥብቅ ይታመንበታል። የዚህን ተፈላጊነት ከተገነዘቡት የአፍሪቃ ሃገራት መካከል የተጫፈሩ ደሴቶችን ያቀፈችው ካቡ ቬርደ(ኬፕ ቨርድ)ከዚህ ሳምንት መግቢያ አንስቶ ክፍለ ዓለሙን የሚያጠቃልለውን የአፍሪቃ የአዳዲስ ግኝቶች ነክ የመሪዎች ጉባዔ የተሰኘውን ዐቢይ ስብሰባ አዘጋጅታ በማካሄድ ላይ ትገኛለች።

Computerunterricht im SOS Kinderdorf in Sambia

ከእቅዱ አንስቶ እስከ ተግባራዊነቱ የኬፕ ቨርድ መንግሥት ፤ የከፍተኛ ትምህርት የሳይንስና ግንቶች ጉዳይ ሚንስቴር ፤ ራሱ የሀገሪቱ ብሔራዊ ም/ቤት ፣ የመገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ማሕበር፣ በተለይ ደግሞ ከትምህርት ሚንስቴር ጋር ተባብሮ የሚሠራው IHABA በሚል አሕጽሮት የታወቀው የግንባታ ነክ ኩባንያ ታሳታፊ ሆኗል። በጉባዔው ከተለያዩ የአፍሪቃ የልዩ ልዩ ፈጠራ ውጤቶች ባለሙያዎች ጋር የዕውቀትና ልምድ ልውውጥ ተፈላጊነት ልዩ ግምት እንደተሰጠው ለማወቅ ተችሏል። ባለፈው ቅዳሜና እሁድ

New Partnership for Africa's Development | NEPAD

ካዘጋጀው የ 2 ቀናት ልዩ ዐውደ ጥናት ጋር ተያይዞ የቀጠለው ዐቢዩ የአፍሪቃ የፈጠራ ጉዳዮች ነክ ጉባዔ እስከ ነገ የሚዘልቅ ሲሆን በጉባዔው ከሚደመጡ ዲስኩሮች ፤ ከሚካሄዱ ውይይቶች ሌላ፣ ዐውደ ርእይ መqቅረቡም ታውቋል ። ለአብነት ያህል፤ ኬንያዊው ኢቫንስ ዋዶንጎ 5o ከመቶ ከሚጣል ሆኖም ሊታደስ ከሚችል ቁሳቁስ የሠሩት ፣ በፀሐይ ኃይል የሚሠራው ፋኖስ መሰል መብራት --

«ቢት ቤይት» የተሰኘው ከአልጀሪያ የቀረበው ለሰው ጠንቅ ሳይሆን፤ አይጥ፣ አንበጣና ሌሎችንም የሰብል ጠንቅ የሆኑነፍሳትን የሚያጠፋው በሥነ ቅመማ የቀረበ የሚራጭ መድኃኒኅት--

ከቶጎ ፣ አርጅተው ከሚጣሉ የኤሌክትሮኒክ ቁሳቁሶች፣ በ 3 ማእዘናዊ መልኩ ማተሚያ መሣሪያ ፣ ሠርቶ ማቅረብ የተቻለበት ሁኔታ፤--

ከጋምቢያ ፣ በቀላል ዋጋ ለምግብ ማብሰያ የሚሆን ታዳሽ የኃይል ምንጭ ማቅረብ የተቻለበት ዘዴ ፤ እነዚህንና የመሳሰሉትን ፣ ለምሳሌ ያህል መጥቀስ ይቻላል።

(ይቀጥላል)

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic