የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ጉባኤ | አፍሪቃ | DW | 12.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ጉባኤ

በ2017 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ የነበረችው ሊቢያ በሃገሪቱ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እድሉን ለሌሎች ሃገሮች ለመስጠት ተገዷል።ኢትዮጵያ፤ኬንያና ጋና ደግሞ የውድድሩን የማዘጋጀት እድል ለማግኘት የመጨረሻውን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ናቸው

default

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዓመታዊውን ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዛሬ ጀመረ።አህጉራዊውን ውድድር በበላይነት የሚመራውና በካሜሮናዊው ኢሳ ሃያቱ የሚመራው አህጉራዊ ተቋም በጉባኤው መጨረሻ የ31ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሃገር ይመርጣል።እሸቴ በቀለ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ኢትዮጵያ አህጉራዊውን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ካዘጋጀች 38 አመታት ተቆጠሩ። እ... 1976 .. የተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለኢትዮጵያ የመጨረሻዋ ይሁን እንጂ ከዚያ በፊት ሦስተኛውን ና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች የደገሰችው ኢትዮጵያ ነበረች።ሶስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማሸነፍ የቻለችው ኢትዮጵያ ከግብጽና ሱዳን ጋር ከመሰረተችው አህጉራዊ ውድድር በተሳትፎና ዝግጅት ርቃ ቆይታለች። ከ31 አመታት በኋላ ደቡብ አፍሪካ ላይ በተዘጋጀው 28ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወደ ተሳትፎ የተመለሰችው ሃገር አሁን ደግሞ የአስተጋጅነት እድሉን ለማግኘት የመጨረሻ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እ... 20172019 እና 2021 ለሚካሄዱት አህጉራዊ ውድድሮች አዘጋጆችን ለመምረጥና አህጉራዊ የእግር ኳስ ጉዳዮች ላይ ለመምከር አዲስ አበባ ላይ ጉባኤ ተቀምጧል።ከመስከረም 2-11 /2007 በሚቆየው ጉባኤ በአህጉራዊው ውድድር መሰረታዊ ውሳኔዎች ያሳልፋል ሲሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ተናግረዋል።

2017 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ የነበረችው ሊቢያ በሃገሪቱ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እድሉን ለሌሎች ሃገሮች ለመስጠት ተገዷል።ኢትዮጵያ፤ኬንያና ጋና ደግሞ የውድድሩን የማዘጋጀት እድል ለማግኘት የመጨረሻውን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።ኬንያ ውድድሩን ከታንዛኒያ፤ኡጋንዳ ወይም ሩዋንዳ ጋር ለማዘጋጀት አቅዳለች።ኢትዮጵያ የተሻለ መሰረተ ልማትና ስታዲየሞች ካሏቸው ሃገራት ጋር ውድድር ውስጥ የገባችበት የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅነት ውሳኔ መስከረም 10/2007 በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እንደሚወሰን አቶ ወንድምኩን አላዩ ይናገራሉ።

እሸቴ በቀለ

ተክሌ የኋላ