የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት | የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል ሙሉ ይዘት | DW | 24.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ይዘት

የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

ከ 50 ዓመት በፊት፤ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት (አ አ ድ) ተመሠረተ። እ ጎ አ በ 2002 ተከታዩ የሆነው ድርጅት ፤ የአፍሪቃ ኅብረተ ተተካ። ቀጥሎ የሚቀርበው ስዕላዊ ዘገባ ፤ የአፍሪቃን አንድነት ድርጅት የ 50 ዓመት ታሪክ በአጭሩ የሚዳስስ ነው።

ስዕል 1 አንዲትሴት፤በከፍተኛውየሥልጣንሠገነት 16531937

እጎአበ2002 እንኮሳዛናድላሚኒዙማየመጀመሪያቱአንስታይጾታየኮሚሽኑፕሬዚዳንት ይሆኑዘንድተመረጡ።ይህየአፍሪቃኅብረትእጅግከፍተኛውየሥልጣንቦታነው።የቀድሞዋየደቡብ አፍሪቃየሀገርአስተዳደርሚንስትር በአፍሪቃኅብረትአዲስ የአሠራርመንፈስ ማሥፈናቸውን ያሣለፏቸውን100 የሥልጣንቀናትየገመገሙታዛቢዎችመሥክረዋል።ግንቦት17 ቀን2005 የተለያዩ53 ሃገራትንያቀፈውድርጅትየተመሠረተበትን 50ኛዓመትያከብራል።

ስዕል 2 መከፋፈልንለማስቀረት አንድነት 16817443

የአፍሪቃ አንድነትድርጅትግንቦት17 ቀን 1955 ዓምሲመሠረት ያኔሁሉምየክፍለ-ዓለሙ 30 ው ነጻመንግሥታትተሳትፈውነበረ።የፖለቲካውየጋራስምምነት፤የአፍሪቃንመከፋፈልመግታትችሏል።

በቀዝቃዛውጦርነትወቅት፤ፀረቅኝአገዛዝንቅናቄዎች፤በኃያላንመንግሥታትተጽእኖ በመፍቀሬናጸረምዕራብአቋምየተከፋፈሉነበሩ። ቀጥሎየሚታየውየመሪዎችፎቶግራፍ በ1958 ዓምየተነሣነው።

ስዕል 3 የ «ፓንአፍሪካኒዝም» ጠንሳሾች 16817436

ክዋሜ ንክሩማ(በስተግራ) -የመጀመሪያው የጋና ፕሬዚዳንት ፤ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ (መኻል) ሁለቱም ግንባር ቀደም የአፍሪቃ አንድነት አባቶች የሚባሉ ናቸው። አፍሪቃ አቀፍ ኅብረት ይሉ የነበሩት ንክሩማ «የተባበሩ የአፍሪቃ ግዛቶች»ን የመመሥረት ዓላማን ነበረ የሚያራምዱት። ይህ ፤ በቅኝ ገዥዎች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ለመውሰድ፣እንዲሁም የጋራ ገበያ ለመመሥረት ይበጃል የሚል አመለካከት ነበራቸው። ይሁንና በቅርብ ነጻነታቸውን ተጎናጽፈው የነበሩት ሃገራት ያን ያህል ርቆ ለመሄድ ፍላጎቱ አልነበራቸውም።

ስዕል 4 የጋራው ባላንጣ፤ 16817 532

በአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የመጀመሪያዎቹ 10 ዓመታት፣ እጅግ ጠቃሚውና በቂ ምክንያትም የነበረው የፖለቲካ አጀንዳ፣ ዘረኛውን የደቡብ አፍሪቃ ሥርዓት መታገል ነበር። እንዲያውም፤ ድርጅቱ ሲመሠረት በዚያው ወቅት ነው የነጻ አውጭ ኮሚቴ የተቋቋመው። እ ጎ አ ከ 1970 አንስቶ በዘረኛው የአፓርታይድ መንግሥት ላይ ይካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ይደግፍ ነበር።

ስዕል 5 ለኤኮኖሚ ዕድገት አዲስ እመርታ፤ 16676698

እ ጎ አ በ 1980 የሌጎስ ተግባራዊ አቅድ በተሰኘው መርኅ፤ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት፤ ለአፍሪቃ የኤኮኖሚ ዕድገት ማንቀሳቀሻ መላውን ነበር ለማቅረብ የፈለገው።

በዚያ የተደረገው ስምምነትም፤ እ ጎ አ እስከ 2000 ዓ ም፤ የጋራ ገበያ ለመመሥረት ነበረ ትኩረቱ። ይሁንና እንዲሁ አቅድ ሆኖ ነው የቀረው። እ o አ በ 1991 የቀጠለው የአቡጃ ስምምነት እ ጎ አ እስከ 2025 የአፍሪቃ የጋራ የኤኮኖሚ ማኅበር እንዲመሠረት ነው የተለመው።

ስዕል 6 አከራካሪ የነጻነት ፖለቲካ፤ 15807405

የድርጅቱ መተዳደሪያ መሠረታዊ መርኅ፣ የግዛት ወሰኞች ሳይለወጡ በዚያው እንዲቆዩ ይሆናል የሚል ነው። እ ጎ አ በ 1982 ፖሊሳሪዮ፣ ያቋቋመውን ዴሞክራቲክ ዐረብ ሰሃራዊ ሪፓብሊክ የተባለውን የምዕራባዊት ሰሐራ መንግሥት የአፍሪቃ ኅብረት ተቀበለ። ሞሮኮ በዚህ ተናዳ ከአባልነት ራሷን አገለለች። እስካሁን ከድርጅቱ ራሷን ያገለለች ብቸኛይቱ አፍሪቃዊት ሀገርም ናት፣ሞሮኮ።

ስዕል 7 ነቀፌታ በመንግሥታቱ ማኅበር ላይ 16818974

የአፍሪቃ ኅብረት በምዕራባዊት ሰሃራ ጉዳይ በተናጠል የፖለቲካ አቋም የወሰደበት ሁኔታ ነበረ። በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት በሚለው መመሪያው፣ በሩዋንዳ ህዝብ ሲጨፈጨፍ ዝም ብሎ ነበረ የተመለከተው። ምሁራን፤ በያመቱ በአዲስ አበባ ይካሄድ የነበረውን ጉባዔ የአምባገነኖች ክለብ እያሉ መዝለፍን ነበረ የሚመርጡት። አንዱ ነቃፊ የእ ጎ አ በ 1986 በዩጋንዳ ሥልጣን የጨበጡት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ነበሩ።

ስዕል 8 የተጠሉት ወታደሮች፤ 16818907

እ ጎ አ በ 1990ኛዎቹ መግቢያ፣ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አዲስ ፖለቲካ ቀየሰ። አፍሪቃ በውስጡ ለሚፈጠሩ ውዝግቦች ራሱ መላ መሻት ፍላጎቱ መሆኑን ገለጠ። ለዚህም ተብሎ ለሰላም የሚያስገድዱ እርምጃዎች ተቀናበሩ። በቡሩንዲ ፤ እ ጎ አ በ 1996 ወታደሮች መፈንቅለ መንግሥት ሲያደርጉ፣ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት፤የእገዳ

እርምጃዎችን ወሰደ። ሆኖም ሰላም ማስከበሪያው እርምጃ በገንዘብ እጦት ጭምር ደካማ ነበረ።

ስዕል 9 ምን ያህል ጊዜ ራስን መከላከል፤ 1682 1093

በአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አስፈንዳቂ ደስታ የተንጸባረቀው ድርጅቱ ከተመሠረተ ከ 30 ዓመት በኋላ ፣ እ ጎ አ በ 1994 ደቡብ አፍሪቃ የድርጅቱ አዲስ አባል ስትሆን ነበረ። ባሁኑ ጊዜ ድቡብ አፍሪቃ አዲስ አበባ ውስጥ ጠቃሚ ድርሻ በማበርከት ላይ ናት። አንዳንዶች እንደሚሉት እጅግ የገዘፈ ድርሻ ነው ያላት።

ስዕል 10 የአዲስ ዘመን ጅምር፤ 15699212

በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ፍጻሜ ደቡብ አፍሪቃ፣ ከዘር አድልዎው ሥርዓት (አፓርታይድ) ከተላቀቀች በተለይም እ ጎ አ ከ 1999 አንስቶ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አዲስ እንቅሥቃሴ ተንጸባርቆበታል። የሊቢያው መሪ ሙኧመር ጋዳፊ፤ (እዚህ ላይ በ 2006 በተካሄደ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ነው የሚታዩት)አፍሪቃ አቀፍ ንቅናቄ (ፓን አፍሪካኒዝም ) የተሰኘውን «የተባበሩት የአፍሪቃ ግዛቶች» መንፈስ አነቃቅተው ነፍስ ሊዘሩበት ሞክረው ነበር። በነበራቸው ሀብት በመጠቀም ነበረ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የፈለጉት። ለብዙ አገሮችም የአባልነት ክፍያቸውን ጋዳፊ ነበሩ የሚሸፍኑላቸው።

ስዕል፤ 11 ከ አ አ ድ ወደ አ ኅ፣ 16821126

ጋዳፊ የሆነው ሆኖ አልተሳካላቸውም። እንዲያውም እቅዳቸው ድርጅቱ በደርባን ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ፤ የአፍሪቃ ኅብረት ሲባል አባላቱ በሀሳብ ከሁለት እንዲከፈሉ አድርጎ ነበር ። የአፍሪቃ ኅብረት ሲመሠረት፤ በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት የሚለው የፖለቲካ መርኅ እንደገና አንሠራራ። ኅብረቱ ሲመሠረት የነበረው ስብሰባ--

ስዕል 12 አቅም የለሽ ተቋም 16819541

የአፍሪቃ ኅብረት መዋቅሩ የአውሮፓውን ኅብረት የተከተለ ነው። አፍሪቃ አቀፍ ፓርላማ እንዲመሠረትም ነበረ ያኔ የተወሰነው። እ ጎ አ በ 2004 ከ 47 አገሮች የተውጣጡ 235 ተወካዮች ተመደቡ። የፓርላማ ተወካዮቹ አዳራሽ የሚገኘው ሚድራንድ በተባለችው የደቡብ አፍሪቃ ንዑስ ከተማ ነው። አዲስ አበባ ከሚገኘው ከማዕከላዊው የአፍሪቃ ኅብረት መ/ቤት መራቁም ፤ የሚያመላክተው፤ የፓርላማ አባላቱ የፖለቲካ ተጽእኖ ማሣረፍ እንደሚቻላቸው ነው።

ስዕል 13 አዲስ እርምጃ ለሰላም 16819559

በአዲሱ ምዕተ ዓመት 20 ከመቶው አፍሪቃውያን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የኃይል እርምጃ ያጀባቸው ውዝግቦች ህይወታቸው በመነካቱ፤ የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም ማሥፈን ለሚቻልበት ተግባር ዐቢይ ትርጉም ሰጥቶታል። እ ጎ አ በ 2004 የሰላምና ጸጥታ ም/ቤት ያቋቋመውም ለዚህ ነው። ጣልቃ ገብቶ መላ የሚሻ ኃይል መላክም ተፈላጊ ሆኖ ተገኘ። በዚያው ዓመትመ ነበረ የአፍሪቃ ኅብረት፣ ለሱዳኑ የዳርፉር ክፍለ ሀገር ህዝብ ደኅንነት የራሱን ሰላም አስከባሪ ጦር ኃይል የላከው።