የአፍሪቃ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቃጠና ትግበራና ፈታኝ ድርድሮች  | ኤኮኖሚ | DW | 05.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የአፍሪቃ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቃጠና ትግበራና ፈታኝ ድርድሮች 

የአፍሪቃ አኅጉራዊ የንግድ ቃጠና ተግባራዊ ለመሆን የሚያስፈልገው መስፈርት ተሟልቶ ሥራ ላይ ውሏል። ለአባል አገሮች ያለ ገደብ አሊያም እጅግ አናሳ በሆነ ገደብ እንዲገበያዩ እድል የሚሰጠው የአፍሪቃ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቃጠና ፈታኝ ድርድሮች ይጠብቁታል። ምን አይነት ድርድሮች ይደረጋሉ? ስምምነቱን ያልፈረሙት ኤርትራ፣ ናይጄሪያና ቤኒን ምን ያጣሉ?

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:00

ከፕሮፌሰር ፕሮፌሰር መላኩ ጎብዬ ጋር የተደረገው ቃለ-መጠይቅ

ኢትዮጵያን ጨምሮ በ24 አገሮች የጸደቀው የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ባለፈው ግንቦት 22 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. የታቀደው ከተሳካ ነጻ የንግድ ቀጠናው አጠቃላይ ዓመታዊ የምርት መጠናቸው 2.5 ትሪሊዮን የሚደርስ 1.2 ቢሊዮን ሸማቾች ይኖሩታል።
በዩናይትድ ኪንግደም የሌስተር ደ ሞንትፎርት ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ኤኮኖሚና የሕግ ፕሮፌሰሩ ፕሮፌሰር መላኩ ጎብዬ አሁን "እነዚህ 24 አገሮች የሚያመርቷቸውን እቃዎች ያለ ምንም ገደብ ወይም በጣም አናሳ በሆነ ገደብ እርስ በርስ መነገድ ይችላሉ" ሲሉ ፋይዳው ላቅ ያለ እንደሆነ ይናገራሉ። 
የንግድ ቃጠናው በስኬት ተግባራዊ ከተደረገ የአፍሪካ የማምረቻ ዘርፍ በእጥፍ አድጎ በጎርጎሮሳዊው 2025 ዓ.ም. አንድ ትሪሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሸቀጦች ማምረት እና ለ14 ሚሊዮን የአኅጉሪቱ ዜጎች የሥራ ዕድል ሊፈጥር ይችላል የሚል ቅድመ-ግምት ተቀምጧል። 
ስምምነቱ በተፈረመ በጥቂት ወራት ውስጥ 24 አገሮች በየምክር ቤቶቻቸው አፅድቀው ወደ ሥራ ቢገባም የንግድ ቀጠናው ከፊቱ ፈታኝ ድርድሮች ይጠብቁታል። ፕሮፌሰር መላኩ እያንዳንዱ አገር በተወካዮቻቸው አማካኝነት ቀረጥ በሚከፈልባቸው ዝርዝር እቃዎች ላይ ድርድር ማድረግ እንደሚጠብቃቸው ይናገራሉ። ድርድሩ ለሸቀጦች እና አገልግሎቶች ተብሎ ለሁለት የተከፈለ ነው። 

ከፕሮፌሰር ፕሮፌሰር መላኩ ጎብዬ ጋር የተደረገውን ቃለ-መጠይቅ ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ
 

እሸቴ በቀለ

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

Audios and videos on the topic