1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና የአውሮጳ ዋንጫ አንድምታዎች

ሰኞ፣ ሰኔ 17 2016

4ኛ ቀኑን ባስቆጠረው እና ካሜሩን ዱዋላ እያስተናገደች በሚገኘው የአፍሪቃ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል። በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 17ኛው የአውሮጳ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጫወታዎች ላይ ደርሷል።

https://p.dw.com/p/4hRVC
Euro 2024 Manuel Neuer Torhüter Deutsche Nationalmannschaft
ምስል Andrzej Iwanczuk/picture alliance

የሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

 

የካሜሩን እያስተናገደች በምትገኘው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 17ኛው አውሮጳ ላይ ዉጤቶች አጠቃላይ አንድምታው ላይ ያተኮሩ መረጃዎች ተካተውበታል።

4ኛ ቀኑን ባስቆጠረው እና ካሜሩን ዱዋላ እያስተናገደች በሚገኘው የአፍሪቃ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን  እየተሳተፈ ይገኛል። በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ የሆኑባቸው ውድድሮችም ተካሂደዋል።

በውድድሩ 5000 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል። ፋንታዬ በላይነህ  በርቀቱ አንደኛ በመሆን  የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ለሀገሯ አስገኝታለች። ውብርስት አስቻል ደግሞ በውድድሩ ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊያውን ወስዳለች። ውድድሩ ቀጥሎ ትናንት እሁድ በተካሄደ የወንዶች  10000 ሜትር  በተመሳሳይ ኢትዮጵያውያን ተከታትለው በመግባት የወርቅ እና የብር ሜዳሊያውን አሸንፈዋል። ውድድሩን ንብረት መላክ አሸንፎ የወርቅ ሜዳሊያ ውን ሲወስድ ገመቹ ዲዳ ደግሞ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ውድድሩ ቀጥሎ ሲካሄድ ዛሬ ምሽት አትሌት ገላ ሀብሴ እና አትሌት አለም ንጉስ የሚወዳደሩበት የ10ሺ ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ይካሄዳል።የ2016 ዓ.ም የአውሮፓ ዋንጫ መክፈቻ እና የጀርመን ድል

ከዚሁ ከአትሌቲክስ ዜና ሳንወጣ ትናንት እሁድ  በፖላንድ በተካሄደው የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ የሴቶች ሩጫ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ሐይሉ አሸንፋለች፡፡ ፍሬወይኒ ውድድሩን ለማሸነፍ 3፡58.59 ወስዶባታል።

አሜሪካ ቦስተን ባስተናገደችው ሌላው የሴቶች የ10 ሺ ሜትር የሩጫ ውድድው ኢትዮጵያውያን አትሎቶች ከ 1 እስከ 3  ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

ውድድሩን መልክናት ዉዱ ቀዳሚ ሆና ስታሸንፍ የገባችበት ሰዓት በ31 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ ሆኗል። ቦሰና ሙላት በ31 ደቂቃ ከ16 ሴኮንድ ሁለተኛ እንዲሁም ሰናይት ጌታቸው በ31 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ በመግባት 3ኛ ወጥታለች።

ኢትዮጵያውያን ያሸነፉባቸው የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች እና የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፍጻሜ

17ኛው የአውሮጳ ዋንጫ

በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 17ኛው የአውሮጳ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጫወታዎች ላይ ደርሷል። በመላው ጀርመን ከተሞች የጀርመን እና የሌሎች በውድድሩ እየተሳተፉ የሚገኙ ብሄራዊ ቡድኖች ደጋፊዎች ልዩ ድባብ መፍጠራቸውን ቀጥለዋል። የዶይቼ ቬለ የአማርኛው ክፍል ጋዜጠኞች ወደ ተለያዩ ከተሞች ተጉዘው ድባቡን ተመልክተዋል። 

የእግር ኳስ ደጋፊዎች ድባብ በፍራንክፈርት
በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 17ኛው የአውሮጳ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጫወታዎች ላይ ደርሷል። በመላው ጀርመን ከተሞች የጀርመን እና የሌሎች በውድድሩ እየተሳተፉ የሚገኙ ብሄራዊ ቡድኖች ደጋፊዎች ልዩ ድባብ መፍጠራቸውን ቀጥለዋል። ምስል Arne Dedert/dpa/picture-alliance

በምድብ አንድ ጀርመን እና ስዊዘርላንድ በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፍ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ስኮትላንድ ከውድድሩ ስትሰናበት ሀንጋሪ ጥሩ ሶስተኛ ሆና ለማለፍ የሌሎቹን ውጤት ትጠብቃለች። እሁድ ምሽት 4:00 ሰዓት በተደረጉ ሁለት ጫወታዎች ጀርመን ከስዊዘርላንድ 1-1 እንዲሁም ሀንጋሪ ስኮትላንድን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ብርቱ የመሸናነፍ ፍልሚያ በተደረገበት የጀርመን እና ስዊዘርላንድ ጫወታ ግብ በማስቆጠር ስዊዘርላንዶች ቀዳሚ ነበሩ።

የጀርመኑ አጥቂ አቻ የምታደርገውን ጎል አስቆጥሯል
በምድብ አንድ ጀርመን እና ስዊዘርላንድ በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፍ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።ምስል Julia Rahn/Pressefoto Baumann/picture alliance

ለስዊዘርላንድ ዳን ንዶዬ በ28ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር ፤ ለጀርመን ተቀይሮ የገባው ኒክላስ ፉልክሩግ በ92ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል። በዚህም ሰባት ነጥቦች የሰበሰበችው ጀርመን ምድቡን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ አምስት ነጥቦች የያዘችው ሲዊዘርላንድ ሁለተኛ በመሆን በቀጥታ ጥሎ ማለፉ ተቀላቅላለች። ስኮትላንድ ከውድድሩ መሰናበቷን ያረጋገጠች ሁለተኛ ሀገር ሆናለች። ሀንጋሪ ጥሩ ሶስተኛ ሆና የማለፍ ዕድል ሊኖራት ይችላል።

የስዊዘርላንድ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች
ለስዊዘርላንድ ዳን ንዶዬ በ28ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር ፤ ለጀርመን ተቀይሮ የገባው ኒክላስ ፉልክሩግ በ92ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።ምስል Peter Klaunzer/KEYSTONE/picture alliance

ለአውሮጳ እግር ኳስ ጨዋታ ውድድር የጀርመን ቡዱን ዝግጅት

የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጫወታዎች ዛሬ ምሽት  ቀጥለው ሲካሄዱ በምድብ ሁለት የሚገኙት ኔዘርላንድ ከአልባንያ እንዲሁም ጣልያን ከክሮሽያ በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት 4:00 ሰዓት ይጫወታሉ። ምድቡን አስቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው ስፔን በስድስት ነጥብ ስትመራ ጣልያን በ3 ነጥብ ትከተላለች። አልባንያ እና ክሮሽያ እኩል አንድ አንድ ነጥብ ይዘዋል። ከምድቡ ሁለተኛ ሆኖ የሚያልፈው ሀገር በጥሎ ማለፉ ከጀርመን ጋር የሚጫወት የሆናል።  

EURO 2008 - Spielball für das Finale
የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጫወታዎች ዛሬ ምሽት  ቀጥለው ሲካሄዱ በምድብ ሁለት የሚገኙት ኔዘርላንድ ከአልባንያ እንዲሁም ጣልያን ከክሮሽያ በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት 4:00 ሰዓት ይጫወታሉ።ምስል Kerim Okten/EPA/picture alliance

ባለፈው አርብ የተጀመረው በአሜሪካ አስተናጋጅነት እየተካሄዱ ያሉ  የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድሮች ትናንት እና ዛሬ ቀጥለው ሲደረጉ ቬንዙዌላ ኢኳዶርን 2 ለ  1 እንዲሁም ሜክሲኮ ጃማይካን 1 ለ 0 አሸንፈዋል። ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጫወታዎች ደግሞ አሜሪካ ቦሊቪያን 2 ለ 0 እንዲሁም ዩራጋይ ፓናማን  3 ለ 1 አሸንፈዋል። ባለፈው አርብ በተካሄዱ ጫወታዎች አርጀንቲና ካናዳን 2 ለ 0 እንዲሁም ፔሩ እና ቺሊ ያለግብ ተለያይተዋል። ጫወታው ነገ ቀጥሎ ሲካሄድ ኮሎምቢያ ከፓራጓይ እንዲሁም ብራዚል ከኮስታሪካ ይጫወታሉ ። በውድድሩ አ,ስራ ስድስት ሀገራት እየተካፈሉበት ይገኛሉ። እንግዲህ አድማጮቻችን ለዛሬ ያልነው ስፖርታዊ መሰናዷችንም ይህንኑ ይመስላል ፤ ሳምንት በሌሎች ስፖርታዊ መረጃዎች እንጠብቃችኋለን ። እስከዚያው ቸ,ር እንሰንብት ።

ታምራት ዲንሳ 

ነጋሽ መሐመድ