የአፍሪቃ ና የደቡብ አሜሪካ መሪዎች ጉባኤ | ዓለም | DW | 21.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአፍሪቃ ና የደቡብ አሜሪካ መሪዎች ጉባኤ

የደቡብ ደቡብ ሃገሮች ህብረት ባለፉት 4 አመታት ይህን ነው የሚባል ተጨባጭ ውጤት ባለማሳየት ይተቻል ። በሌላ በኩል 2 ተኛውን ጉባኤ ያደመቁት ፣ 3 ቱ መሪዎች በአሁኑ ጉባኤ ላይ አለመገኘታቸው የነውን ጉባኤ ያቀዘቅዛል የሚል ፍራቻ አሳድሯል ።የደቡብ-ደቡብ ትብብር የተሠኘዉ ማሕበር የሚያስተናብራቸዉ የአፍሪቃና የደቡብ አሜሪካ ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ ነገ ማላቦ-ኢኳቴሪያል ጊኒ ዉስጥ ይጀመራል።በጉባኤዉ ላይ የሐምሳ አራቱ የአፍሪቃ ሐገራት መሪዎች ከአስራ-ሁለቱ የደቡብ አሜሪካ ሐገራት አቻዎቻቸዉ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ።የደቡብ ደቡብ ትብብር የተሰኘዉ ማሕበር ከተመሠረተ ወዲሕ የሁለቱ ክፍለ-ዓለማት መሪዎች ሲሰበሰቡ የነገዉ ሰወስተኛቸዉ ይሆናል።የማሕበሩ አለማ የሁለቱን ክፍለ ዓለማት ምጣኔ ሐብታዊ ትብብር ለማጠናከርና ለመረዳዳት እንደሆነ የአባል ሐገራት መሪዎች በየጊዜዉ ይናገራሉ።ቻተምሐዉስ የተሰኘዉ የብሪታንያ የጥናት ተቋም ባልደረባ አሌክስ ቫይነስ እንደሚሉት ግን ትብብሩም ሆነ ጉባኤዉ ፖለቲካዊ ነዉ።«ጉባኤዉ እንደሚመስለኝ ፖለቲካዊ ነዉ።የደቡብ ደቡብ ትብር ርዕዮተ-ዓለም ነዉ።ጥሩ ምሳሌዎች አሉ።ብራዚል የእርሻ ምርታማነትን ለማሳደግና የቆላ በሽታዎች መከከላከያ መድሐኒቶችን ለአፍሪቃዉያን ታካፍላለች።ከዚሕ ባለፍ ለምስሌ ቬኑዜዋላ ዓለማ ፖለቲካዊ ነዉ።»

ከዚሕ ቀደም እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በሁለት ሺሕ ስድስትና በሁለት ሺሕ ዘጠኝ በተደረጉት ሁለት ጉባኤዎች ላይ የሊቢያ፥ የብራዚልና የቬኑዝዌላ መሪዎች ይዘዉት የነበረዉ አቋም ጉባኤዎቹ የዓለምን ትኩረት እንዲስቡ አድርገዉ ነበር።ዘንድሮ ግን የሊቢያዉ መሪ ተገድለዋል።የቬኑዙዌላዉ ታመዋል።የብራዚሉ ጡረታ ወጥጠዋል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic