የአፍሪቃ ና የአውሮፓ የኤኮኖሚ ግንኙነት | ኤኮኖሚ | DW | 09.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የአፍሪቃ ና የአውሮፓ የኤኮኖሚ ግንኙነት

በአሁኑ ወቅት የአፍሪቃና የአውሮፓ የኤኮኖሚ ግንኙነት አዲስ አቅጣጫ እንዲከተል ያስፈለገበት ምክንያትና ጥቅሙ ምንድነው ? የኤኮኖሚ ግንኙነቱ በሁለቱ ክፍለ ዓለማት የፖለቲካና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይስ ምን ዓይነት ተፅእኖ ያሳድራል ?ከኤኮኖሚው ዓለም የሚያነሳቸው ጉዳዮች ናቸው ።

ባለፈው ሳምንት ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ የተካሄደው አራተኛው የአፍሪቃ የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተነጋግሮ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች ውስጥ የሁለቱ ክፍለ ዓለማት የኤኮኖሚ ግንኙነት አንዱ ነበር ። የመሪዎቹ ጉባኤና እዚያው ብራስልስ የተካሄዱ ሌሎች ተጓዳኝ ስበስባዎች የሁለቱን ክፍለ ዓለማት የኤኮኖሚ አጋርነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲሁም ኤኮኖሚያቸውን ለማሳደግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን በመተለም ተጠናቀዋል ። በአሁኑ ወቅት የአፍሪቃና የአውሮፓ የኤኮኖሚ ግንኙነት አዲስ አቅጣጫ እንዲከተል ያስፈለገበት ምክንያትና ጥቅሙ ምንድነው ? የኤኮኖሚ ግንኙነቱ በሁለቱ ክፍለ ዓለማት የፖለቲካና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይስ ምን ዓይነት ተፅእኖ ያሳድራል ? የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ በዛሬው ከኤኮኖሚው ዓለም ዝግጅት ከሁለቱ ክፍለ ዓለማት መሪዎች ጉባኤ ውሳኔዎችና መግለጫዎች ጋር እያገናዘበ የሚዳስሳቸው ጉዳዮች ናቸው ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic