የአፍሪቃ ኅብረት የኮሚሽን ምርጫ | አፍሪቃ | DW | 04.07.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የአፍሪቃ ኅብረት የኮሚሽን ምርጫ

የአፍሪቃ ኅብረትን ኮሚሽን ፕሬዝደንት ለመምረጥ ተከታታይ ዉይይቶች በመካሄድ ላይ ናቸዉ። ከአዉሮጳዉያኑ 2008ዓ,ም ጀምሮ የኮሚሽኑ ፕሬዝደንት የነበሩት ዣን ፒንግን ስፍራ ለመረከብ ደቡብ አፍሪቃ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ

ዘገባዎች ያመለክታሉ። ኅብረቱ ይህን የኃላፊነት መንበር በፆታ ድልድል የማፈራረቅ መመሪያ ቢኖረዉም፤ የደቡብ አፍሪቃ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይቲ ናኮና ማሻባኔ ለደቡብ አፍሪቃ ሀገሮች የልማት ማኅበረሰብ እንደጠቆሙት ላለፉት 49ዓመታት ይህን አላደረገም። ፉክክር ለበዛበት ለዚህ የኃላፊነት መንበር በመጪዉ ሳምንት የሚጀመረዉ የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ እልባት ያገኝለታል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለም አዲስ አበባ በሚገኘዉ የኅብረቱ ጽሕፈት ቤት ዲፕሎማቶች በዚሁ ላይ ምክክር ይዘዋል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ሒሩት መለሠ

Audios and videos on the topic