የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚደንት አምስት እጩዎች  | አፍሪቃ | DW | 12.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚደንት አምስት እጩዎች 

ባለፈዉ ሳምንት ማለቂያ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ዉድድር አካሂዶል። ኅብረቱ ተሰናባቿን የኮሚሽኑን ፕሬዚዳንት ድላሚኒ ዙማን ለመተካት ኅብረቱ ዉድድሩን ያካሄደዉ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በዝግ ጉባኤ አልነበረም።

 

የቀረቡት አምስት እጩዎች በተዘጋጀላቸዉ መድረክ ራዕያቸዉን በይፋ ያስተዋወቁ ሲሆን የአፍሪቃን መልከዓ ምድርና ቋንቋ መሠረት በማድረግ ሁለት ከእንግሊዘኛ፤ ሁለት ከፈረንሳይኛ እንዲሁም አንድ እጩ ከፖርቱጋል ቋንቋ ተናጋሪዎች እጩዎች ናቸዉ የቀረቡት። የቦትስዋናዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔሎኖሚ ቬንሶን ሞይቶቲ ፤ የቻድ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሳ ፋኪ ማህማት፤ የኤኳቶሪያል ጊኒ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አጋፒቶ ማባ ሞኩዩ ፤ የኬንያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና ሞሃመድ እንዲሁም በተመድ የማዕከላዊ አፍሪቃ የቀድሞ ልዩ መልክተኛ እና የሴኔጋል የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር አብዶላዬ ባቲሊ በመድረኩ የየግል ሃሳባቸዉን ለማቅረብ የተፈቀደላቸዉ ሦስት ሦስት ደቂቃ ብቻ እንደነበር በዚህ ዝግጅት ላይ የተገኘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን አመልክቶዋል።


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

Audios and videos on the topic