የአፍሪቃ ኅብረት እና የጀርመን ስምምነት | አፍሪቃ | DW | 08.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የአፍሪቃ ኅብረት እና የጀርመን ስምምነት

ጦር መሣሪያዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር ለኹለት ቀናት የዘለቀ ውይይት በአፍሪቃ ኅብረት ጽ/ቤት ተከናውኗል። በተጠናቀቀው ውይይት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የተባበሩት መንግሥታት ጽ/ቤቶች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የአካባቢው አባል ሃገራት ተወካዮች እና ተመራማሪዎች ተካፋይ ሆነዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:28

የአፍሪቃ ኅብረት እና የጀርመን የጋራ ትብብር

በአፍሪቃ የሣህል ግዛት በተባለው ሰፊ አካባቢ የነፍስ ወከፍ ጦር መሣሪያዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር እና የኅብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ የአፍሪቃ ኅብረት ከጀርመን መንግሥት ጋር አብረው እየሠሩ ናቸው። ውይይቱን በመከታተል እና በጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጦር መሣሪያ ቁጥጥር መምሪያ ኃላፊ ቶማስ ጎይብልን በማነጋገር አዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘገባ ልኮልናል። አብረን እንከታተለው።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic