የአፍሪቃ ችግር፥ የተገባዉ ቃልና የቡድን ሥምንት ጉባኤ | ኤኮኖሚ | DW | 08.07.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የአፍሪቃ ችግር፥ የተገባዉ ቃልና የቡድን ሥምንት ጉባኤ

የአፍሪቃ ችግር፥ የተገባዉ ቃልና የቡድን ሥምንት ጉባኤ

default

የሆካይዶ ጉባኤተኞች

የቀድሞዉ የፈረንሳይ ፕሬዝዳት ቫለሪ ጄስካ ደ ኢስታ በ1975 (ዘመኑ በመሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ራምቡዮ-ፈረንሳይ ላይ የአምስት የሐገራቸዉን ወዳጆች ሐገራት መሪዎች የጋበዙት የነዳጅ ዋጋ ንረት ሥላደረሰዉ የምጣኔ ሐብት ድቀት መላ ለማፈላለግ ነበር።ልክ እንደያኔዉ ነዳጅ ዘይት በተወደደበት፤ የምግብ ዋጋ በናረበት፥ የአፍሪቃ ድሕነት በጠናበት፥የተፈጥሮ ሐብት በተመናመነ-በተበከለበት ዘንድሮ ሥለ-አለም ሊበይኑ ሰኞ ሆካይዶ-ጃፓን ላይ ተሰበሰቡ።-የቡድን ስምት አባል ሐገራት መሪዎች።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።የሆካይዶዉ ጉባኤ መነሻ-የአለም ሁኔታ ማጣቀሻ፥ የአፍሪቃ ችግር መድረሻችን ነዉ አብራችሁኝ ቆዩ።