የአፍሪቃ ተፈጥሮዊ ሐብት | በማ ድመጥ መማር | DW | 22.10.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

በማ ድመጥ መማር

የአፍሪቃ ተፈጥሮዊ ሐብት

በማዳመጥ መማር የተሰኘው የሬድዮ ዝግጅት አፍሪቃውያን ከአካባቢያቸው ጋር ያላቸውን ግንኝነት ይዳስሳል

default

የቀድሞዋ ገነት በመጥፋት ስጋት

አፍሪቃ በዓለም አቀፍ የአየር ብክለት የምታሳድረው ተፅዕኖ በጣም ትንሽ ቢሆንም በአየር ንብረቱ ለውጥ ግን ክፉኛ ተጎድታለች። ከምን ጊዜም በላይ እየጨ መረ የመጣው የሕዝብ ቁጥር የአህጉሪቱ የተፈጥሮ ሀብት በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ መንስኤ ሆኗል።... በማዳመጥ መማር የተሰኘው የሬድዮ ዝግጅት አፍሪቃውያን ከአካባቢያቸው ጋር ያላቸውን ግንኝነት ይዳስሳል...

ደኖች ለግብርና ሲባል ይጨፈጨፋሉ። ሰዎች፤ ዓሳዎችና የዱር እንስሳት ባሉበት ሁሉ እየሄዱ ያድናሉ። ብዙ ከተሞች በቆሻሻ ክምር የሰጠሙ ይመስላሉ። ቆሻሻን ማስወገድ ለአብዛኛው ድሃ የከተማ ሕዝብ ከባድ ነውና:: አሁን ደግሞ አዲስ አደጋ እየተከሰተ ነው። ብዙ አፍሪቃውያን ለመኪና ያላቸው ፍቅር እየጨመረ ነው። ይህ ደግሞ ለዓለማችን የአየር ብክለት የራሱን አስተዋፅዖ እያበረከተ ይገኛል።

የዓለማችን ሁኔታ

የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች መከሰት ጀምሯል። የዝናብ ወቅቶች እያጠሩ ነው:: የሙ ቀቱ መጠን ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መጥቷል። የመጠጥ ውሃ አቅርቦትም እየቀነሰ ነው። ችግሩ ጎልቶ በሚታይበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች የችግሩ ገፈት ቀማሾች እየሆኑ ናቸው። ከዚህ ቀደም ሲያበቅሏቸው የነበሩትን ሰብሎች ሊዘሩ ወደማይችሉበት ሁኔታ ደርሷል። ለመኖር የሚ ያስፈልጋቸው ንፁሕ ውሃም እንዲሁ እየቀነሰ ነው። በተጨማሪም ብርቅዬ የእንስሳትና የዕፅዋት ዝርያ የሚ ገኙባቸው እርጥበታማ ቦታዎችና ደኖች እየጠፉ ይገኛሉ።

አዲስ አቅጣጫ ን መቀየስ

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅታችን ስለአካባቢያችን አንዳንድ እውነታዎችንና የሚ ያጋጥሙ ችግሮች ከማ ስተዋወቁ በተጨማሪ አዲስ አቅጣጫ ን ይጠቁማል። በዝግጅቱ የሚ ቀርበዉ የሬድዮ ጭውውት አራት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አካባብያቸውን ለማወቅ የሚ ያደርጉትን ጥረት ይዳስሳል። ይህም አድማጮች ተማሪዎቹን በመከተል የሚኖሩበትን አካባቢ ለማዳን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲያውቁ በር ይከፍታል።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት በስድስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ፖርቱጋልኛ ይቀርባል። ተጨማሪ መረጃ ወይም ዝግጅቶቹን ደግመው ለማዳመጥ ከፈለጉ እባክዎን

www.dw-world.de/learning-by-ear የተሰኘውን ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ፕሮጀክት በጀርመን ፌደራላዊ የውጪ ጉዳይ ሚ ኒስቴር ይታገዛል።