የአፍሪቃ ቀንድ አለመረጋጋትና የስደተኞች ይዞታ | አፍሪቃ | DW | 07.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የአፍሪቃ ቀንድ አለመረጋጋትና የስደተኞች ይዞታ

ለስደቱ እየተባባሰ መሄድ፣ በሃገራቱ የተለያዩ መንስኤዎች መኖራቸው ቢታወቅም በጥቅሉ ግን ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ ችግሮች በዋነኛ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ዜጎቻቸው ለስደት የሚዳረጉባቸው እነዚህ ሃገራት ደግሞ በርካታ የየጎረቤት ሃገራት ስደተኞችን ተቀብለውም ያስተናግዳሉ።

በርካታ ሰዎች ለስደት ከሚዳረጉባቸው አካባቢዎች አንዱ የአፍሪቃ ቀንድ ነው ። ድርቅ ረሃብና ግጭት ከማይለው ከዚህ አካባቢ የሚሰደደው ህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው። የርስ በርስ ጦርነት የሚካሄድባት ሶማሊያ በሚሰደዱ ዜጎች ቁጥር የመጀመሪያውን ስፍራ ስትይዝ ፣ ግጭት ካልተለያቸው ከ2 ቱ ሱዳኖች የሚሰደዱት ደግሞ 2ተኛውን ደረጃ ይይዛሉ። ከኤርትራን የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥርም ቀላል አይደለም። በንፅፅር ሲታይ ከአካባቢው አገራት የተረጋጉ ናቸው ከሚባሉት ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከኬንያ ሰዎች በብዛት ይሰደዳሉ ። ለስደቱ እየተባባሰ መሄድ፣ በሃገራቱ የተለያዩ መንስኤዎች መኖራቸው ቢታወቅም በጥቅሉ ግን ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ ችግሮች በዋነኛ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ዜጎቻቸው ለስደት የሚዳረጉባቸው እነዚህ ሃገራት ደግሞ በርካታ የየጎረቤት ሃገራት ስደተኞችን ተቀብለውም ያስተናግዳሉ። «የአፍሪቃ ቀንድ አለመረጋጋትና የስደተኞች ይዞታ» የዛሬው የውይይት መድረክ የሚያተኩርበት ርዕስ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲወያዩልን አራት እንግዶችን ጋብዘናል። አቶ ክሱት ገብረ እግዚዘብሔር በኢትዮጵያ የተ መ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣ ዶክተር አልጋነሽ ፍስሃ በአፍሪቃ ቀንድና በሰሜን አፍሪቃ ስደተኞችን የሚረዳ ጋንዲ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሃላፊ፣ የመን በስደት የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም፣ አቶ በቀለ ማሞ በኢትዮጵያ ስደትን ለማስቀረት በግል በግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ የተሰማሩ ናቸው።

ሂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic