የአፍሪቃ ቀንድ ስደትና መፍትሄው | አፍሪቃ | DW | 27.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የአፍሪቃ ቀንድ ስደትና መፍትሄው

ከ 3 ሳምንት በፊት ከሊቢያ በጀልባ ተሳፍረው ወደ ኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ በመጠጋት ላይ ከነበሩ 500 ያህል ኤርትራውያን ከሚያመዝኑባቸው ስደተኞች የ364 ቱ ህይወት ያለፈበት አደጋ በሜዴትራንያን ባህር ላይ እስከ ዛሬ ከደረሱት የሞት አደጋዎች እጅግ የከፋው ነው ።

ከአፍሪቃ ቀንድ እየተሰደዱ ለሞት ለአካል ጉዳት እንዲሁም ለልዩ ልዩ እንግልት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ነው ። በዋነኛነት ከሶማሊያ ከኤርትራና ከኢትዮጵያ የሚሰደዱት ሩቅ አልመው የሱዳንና የሲና በረሃ እንዲሁም የሜዲቴራንያን ባህር ሲሳይ መሆናቸው እየተባባሰ ቀጥሏል ። ድንበር ሲያቋርጡ ፣ በበረሃ እንዲሁም በአደገኛ የባህር ላይ ጉዞ ለሞት ከሚዳረጉት በተጨማሪ እድል ቀንቷቸው በህይወት ካሰቡበት የሚደርሱትም በየሄዱበት በኢሰብዓዊ አያያዝ ይሰቃያሉ ። ስደተኞቹ በሱዳን በየመንና በሊቢያ እስር ቤቶች የሚደርስባቸው በደል በሲና በረሃ የሚፈፀመባቸው ግፍ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ቢስብም ችግሩ እየባሰ እንጂ እየቀነሰ አልሄደም ። ህይወታቸውን ለተለያየ አደጋ አጋልጠው ሰሜን አፍሪቃ ከሚደርሱት ከእነዚሁ ስደተኞች አብዛኛዎቹ በትናንሽ ጀልባዎች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በጉዞ ላይ በሚደርስ አደጋ በተደጋጋሚ ለሞት መዳረግ ከጀመሩ ሰነበቷል ። ከነዚህ አደጋዎች በተለይ ከ 3 ሳምንት በፊት ከሊቢያ በጀልባ ተሳፍረው ወደ ኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ በመጠጋት ላይ ከነበሩ 500 ያህል ኤርትራውያን ከሚያመዝኑባቸው ስደተኞች የ364 ቱ ህይወት ያለፈበት አደጋ በሜዴትራንያን ባህር ላይ እስከ ዛሬ ከደረሱት የሞት አደጋዎች እጅግ የከፋው ነው ። የሚደርስላቸው አጥተው ውሃ የበላቸው የነዚህና ከዛ በኋላም ሆነ በፊት ተመሳሳይ አደጋ የደረሰባቸው ስደተኞች አሳዛኝ እጣ መላውን አለም ሲያነጋግር ከርሟል ። የችግሩ መንስኤ ምንድነው ለአደጋው ተጠያቂው ማነው ? አሁንም ለቀጠለው ይህን መሰሉ ስደትስ ዘላቂው መፍትሄ ምንድነው ? የሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ሰሞኑን ሲነሱና ሲጣሉ ቆይተዋል ። የዛሬው እንወያይም በነዚሁ ነጥቦች ላይ ያተኩራል ። 4 እንግዶችን ጋብዘናል

ሂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic