የአፍሪቃ መሪ ሴቶች ጉባዔ | አፍሪቃ | DW | 27.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የአፍሪቃ መሪ ሴቶች ጉባዔ

የአፍሪቃ መሪ ሴቶች የመረብ ትስስር በሚል ርዕስ በአፍሪቃ ኅብረት ለሦስት ቀናት የተካሄደዉ ጉባዔ ዛሬ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። ሴቶችን በይበልጥ በልማቱ ዘርፍ እና በአፍሪቃ የአመራር ደረጃ ለማብቃት ልዉዉጥ በማድረግ በሚጠናከሩበት ላይ የሚሰራ መሆኑ ተገልፆአል። በተመድ ከወራት በፊት የተደረሰ ስምምነት በቀጣይነት የሚሰራ መረብ መሆኑም ተገልፆአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:27

«ሴቶችን በልማቱ ዘርፍ እና በአመራር ደረጃ ለማብቃት»

የአፍሪቃ መሪ የሴቶች መረብ ትስስር « African Leader  Womens Net-Work»በሚል ርዕስ  ተዋቅሮ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ የታመነበት ከአንድ ወር በፊት ኒዮርክ ላይ በሚገኘዉ በተመድ ዋና ፅፈት ቤት መዋቀሩ ታዉቋል። በአዲስ አበባ በአፍሪቃ ኅብረት ከየአባላቱ የተጋበዙ ሚና ያላቸዉ ሴቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግ በመጠናቀቅ ላይ ያለዉ ጉባዔ ዋና መሰረተ ሃሳቡ ነዉ።

ይህን በዝርዝር የገለፁት በመንግሥታቱ ጽ/ ቤት ምክትል ፀሐፊዋ አሚና መሃመድ ናቸዉ « ይህ የትስስር መረብ በተጠናከረ መልኩ ተዓማኒነት እንዲኖረዉ በሺዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካዉያን ሴቶች የሚሳተፉበት መሆን ይገባዋል በቀጣይ በምንገናኝበት ጊዜ ስለሴቶች በጥቅሉ ለማስረዳት አንደበት ይኖረናል። ህልማችን ተግባራዊ በሚሆንበት ለዝያዉ ለተነሳልነት ዓላማ በየሃገራችን የምንሰራበት ተግባር ነዉ የሚሆነዉ። በጋራ የምንወስደዉ አቅዋም የዉይይት መድረክ መከፈት እንደሚያስፈልግ ነዉ። በሃገራቱ መካከልም ሳይቀር አጋርነትና ዓባልነትንም በማካተት የሴቶችን የመሪነት ሚና በማረጋገጥ በልማት በኤኮኖሚዉ ግችትን ቀድሞ መከላከልን በፖለቲካዉ ተሳትፎ ፤ በአፍሪቃም ሴቶችን ከምርጫ በማግለል እየተደረገ ያለዉን በዚህ ሁሉ ላይ ነዉ የምንሰራዉ።»   የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ቦታዉ ላይ ተገኝቶ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። 

 

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

     

Audios and videos on the topic