የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤና የአሕጉሪቱ ምክር ቤት | ኢትዮጵያ | DW | 28.01.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤና የአሕጉሪቱ ምክር ቤት

ባለሥልጣናቱ እንደሚሉት ምክር ቤቱ በተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት የተደረጉ ምርጫዎች ይታዘባል።የመልካም አስተዳደር ይዞታንም ይገመግማል።

default

የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ሥለ ምርጫ ነፃነትና መልካም አስተዳደር የተረቀቀዉን ሠነድ እንዲያፀድቅ የአፍሪቃ ምክር ቤት ጠየቀ።የምክር ቤቱ መሪዎች ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በሰጡት መግለጫ የፊታችን እሁድ እዚያዉ አዲስ አባባ የሚሰየመዉ የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ሥለ ምርጫ እና ሥለመልካም አስተዳደር ጊዜ ወስዶ እንዲነጋገር ጠይቀዋል።ባለሥልጣናቱ እንደሚሉት ምክር ቤቱ በተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት የተደረጉ ምርጫዎች ይታዘባል።የመልካም አስተዳደር ይዞታንም ይገመግማል።ጌታቸዉ ተድላ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ