የአፍሪቃ ልማትና የውጩ ተጽዕኖ | ኤኮኖሚ | DW | 28.07.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የአፍሪቃ ልማትና የውጩ ተጽዕኖ

አፍሪቃ ከድህነት ለመላቀቅ በምታደርገው ጥረት አሁንም በውጭው ዓለም ዕርዳታ ላይ ጥገኛ ናት።

default

ሆኖም ጥገኝነቱ እየቀነሰና ዕድገቱም እየተፋጠነ በሚሄድበት የተሻለ ዘዴ ላይ የሚካሄደው ውይይት በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት እየጠነከረ ነው የመጣው። የልማት አጋርነቱ ለመሆኑ ከምዕራቡ ዓለም ወይስ ከቻይና ጋር ነው የሚበጀው? ይህ የአፍሪቃ ሕብረት የኤኮኖሚ ጉዳይ ሃላፊ ማክስዌል እምክዌዛላምባም ባለፈው ሰንበት በካምፓላው የመሪዎች ጉባዔ አኳያ ያነሱት ጉዳይ ነበር። ባለሥልጣኑ አፍሪቃ ምዕራባውያን መንግሥታትን በቻይና መተካት ይኖርባታል ብለዋል። ለዚህ እንደ ምክንያት የጠቀሱትም ለምሳሌ በብድር አሰጣጥ ረገድ በዓለም ባንክ በኩል ጭምር ገዳቢ ቅድመ-ግዴታዎችን የሚያስቀምጡ መሆኑን ነው። በአጠቃላይ አፍሪቃ ከምዕራቡ የገንዘብ ጥገኝነት መላቀቅ አለባት ባይ ናቸው። በዚህ ጉዳይ ላይ የኤኮኖሚ ባለሙያ የሆኑትን አቱ እንዳልካቸው ተሥፋዬን አነጋግረናል።

መሥፍን መኮንን
ሂሩት መለሰ