የአፍሪቃ ሁለተኛ ነጻነት? | ኢትዮጵያ | DW | 24.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአፍሪቃ ሁለተኛ ነጻነት?

ከተቋቋመ ሶስተኛ አመቱን የያዘዉ ኢትዮጽያ ጀርመን ፎሩም ኤፋዉ የተሰኘዉ ድርጅት ከትናንት በስትያ ሃሙስ ምሽት በኮለኝ ከተማ «የአፍሪቃ ሁለተኛ ነጻነት? » በሚል አንድ የዉይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በዉይይቱ በአፍሪቃ ስላለዉ ወቅታዊ የፖለቲካ እና የምጣኔ ሃብት እድገት ላይ ሃሳብን አንሸራሽሮአል።

default

አፍሪቃ ቅኝ ግዛትን ለመጨረሻ ግዜ ገርስሳ ከጣለች ከአምሳ አመታት ወዲህ በተለይ ባለፉት ሃያ እና አስራ አምስት አመታት በአፍሪቃ የታየዉ ለዉጥ በምዕራቡ አለም ሊጠቀስ ይገባል የሚሉት የዉይይት መድረኩ ዋና አዘጋጅ አቶ ስጢፋኖስ ሳሙኤል፤ የአፍሪቃ ህብረትም ቢሆን በአፍሪቃ አገራት ዉስጥ የሚያደርገዉ የትብብር ስራ ቀላል አለመሆኑን ገልጸዋል። 350 ያህል ሰዎች የተሳተፉበት ይህ ዉይይት ሶስት አራተኛዉ ተሳታፊ ጀርመናዉያን ሲሆኑ ሌላዉ ኢትዮጽያዉያን እና ጥቂት የሌላ የአፍሪቃ አገር ዜጎች ነበሩ። በዋና ተወያይነት ሶስት ጀርመናዉያን ምሁራን እና ልኡል ዶክተር አስፋዉ ወሰን አስራቴ ተጋባዥ ነበሩ። ዉይይቱን አዜብ ታደሰ ተካፍላ ዘገባ አጠናቅራለች።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን

Audios and videos on the topic