የአፍሪቃዉያን ስደተኞች ጎርፍ በኢጣልያ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 10.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የአፍሪቃዉያን ስደተኞች ጎርፍ በኢጣልያ

ከሊቢያ የባህር ዳርቻ በሜዲተራንያን ባህር በኩል በጀልባ ወደ ደቡባዊ ኢጣልያ ግዛቶች የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ።

የኢጣልያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ባህር ላይ ለአደጋ የተጋለጡ 4000 የጀልባ ስደተኞችን መታደጋቸዉን አስታዉቀዋል። ካለፈዉ ጥር ወር ወዲህ ከሰሜን እና ከመካከለኛዉ ምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት የመጡ በርካታ ስደተኞች ጣልያን መግባታቸዉን የሃገሪቱ የሃገር ዉስጥ አስተዳደር ሚኒስቴር አስታዉቋል። እንደ ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ፤ የሜዲተራንያን ባህር አካባቢ የአየር ፀባይ የተስተካከለ በመሆኑም፤ ከአሁን በኋላም በርካታ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ሜዲተራንያንን አቋርጠዉ ወደ አዉሮጳ ለመግባት ጥርት እንደሚያደርጉ ተገልጿል ፤ ዝርዝሩን ተክለዝጊ ገ/እግዚአብሄር ልኮልናል

ተክለዝጊ ገ/እግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic