የአፍሪቃዉያን ሥደተኞች ችግር በእስራኤል | አፍሪቃ | DW | 10.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የአፍሪቃዉያን ሥደተኞች ችግር በእስራኤል

የእስራኤል መንግሥት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ እስራኤል ገቡ የሚላቸዉን አፍሪቃዉያን ስደተኞች እያስገደደ ወደየሐገራቸዉ መላኩን ቢያቆምም በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ስደተኞች አሁንም ከእስር ቤት በማይሻል ማቆያ ጣቢያ እየማቀቁ ነዉ።ሳሕሩኒም በሚባለዉ በረሐማ አካባቢ በሚገኘዉ ጣቢያ እንዲሠፍሩ ከተገደዱ ስደተኞች መካካል ሕፃናትና ሴቶች ይገኙባቸዋልእስራኤል የሚገኙ የአፍሪቃዉያን በተለይም ኤርትራዉያን ሥደተኞች ከፍተኛ በደል እንደሚፈፀምባቸዉ ሥደተኞቹ እና የመብት ተሟጋቾች አስታወቁ።ሥደተኞችና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እንደሚሉት የእስራኤል መንግሥት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ እስራኤል ገቡ የሚላቸዉን አፍሪቃዉያን ስደተኞች እያስገደደ ወደየሐገራቸዉ መላኩን ቢያቆምም በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ስደተኞች አሁንም ከእስር ቤት በማይሻል ማቆያ ጣቢያ እየማቀቁ ነዉ።ሳሕሩኒም በሚባለዉ በረሐማ አካባቢ በሚገኘዉ ጣቢያ እንዲሠፍሩ ከተገደዱ ስደተኞች መካካል ሕፃናትና ሴቶች ይገኙባቸዋል። ማቆያ ጣቢያ ያልገቡ ሥደተኞችም ሥራ እንዳይሰሩ ይከለከላሉ፥ ይገለላሉም።የሐይፋዉ ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬ ዝር ዝር ዘገባ ሎኮልናል።

ግርማዉ አሻግሬ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች