የአፍሪቃን ቀንድ ያሰጋው ድርቅ | ኢትዮጵያ | DW | 16.07.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአፍሪቃን ቀንድ ያሰጋው ድርቅ

በአፍሪቃ ቀንድ፡ በሶማልያ፡ በኢትዮጵያ፡ በኬንያ፡ በጅቡቲ እና በዩጋንዳ ከአስር ሚልዮን የሚበልጥ ህዝብ አስችኳዩ የምግብ ርዳታ ካልቀረበለት አስከፊ የረሀብ አደጋ እንዳሚያሰጋው ባለፉት ጥቂት ቀናት የወጡ የተመድ ዘገባዎች አስታወቁ።

default

የሶማልያ ስደተኞች በዳዳብ መጠለያ ጣቢያ


በዤኔቭ መረጃዎችን ያቀረቡት የርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ሰራተኞች በተለይ በሶማልያ የተከሰተው ድርቅ እና በዚያ የቀጠለው ውጊያ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው እንዲሸሹ ማስገደዱን እና በህጻናት ላይ ትልቅ ስጋት መደቀኑን አስጠንቅቀዋል። ስግብግብ ነጋዴዎችም አጋጣሚውን በመጠቀም የምግብን ዋጋ እያስወደዱ ትርፍ ለማካበት የሚያደርጉት ጥረታቸው ችግሩን ይበልጡን እያባባሰው መሄዱንም ገልጸዋል።

አርያም ተክሌ
መሰፍን መኮንን

Audios and videos on the topic