የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረቶች ግንኙነት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 25.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረቶች ግንኙነት

ውይታቸው ይበልጥ ያተኮረውም የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረቶችን ግንኙነትና በተለይም በአፍሪቃ ሠላምና ደህንነት ሊረጋገጥ በሚቻላቸው የአሠራር የትብብር መርሃ ግብሮች ላይ ያተኮረ ዶክተር ዙማ አዲሷ የአፍሪቃ ህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ ወዲህ ወደ ብራሰልስ መጥተው

ከህብረቱ ባለሥልጣናት ጋር ሲወያዩ ይህ የመጀመሪያቸው ነው ። የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ዶክተር ድላሚኒ ዙማ ትናንት ብራሰል ውስጥ ከአውሮፓ ህብረት ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ ። ውይታቸው ይበልጥ ያተኮረውም የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረቶችን ግንኙነትና በተለይም በአፍሪቃ ሠላምና ደህንነት ሊረጋገጥ በሚቻላቸው የአሠራር የትብብር መርሃ ግብሮች ላይ ያተኮረ ነበር።ዶክተር ዙማ አዲሷ የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ ወዲህ ወደ ብራሰልስ መጥተው ከህብረቱ ባለሥልጣናት ጋር ሲወያዩ ይህ የመጀመሪያቸው ነው ። ዙማ ትናንት ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሆሴ ኢማኑኤል ባሮሶ ከአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ከክርማን ቫን ሮምፓይ ና ከአውሮፓ ፓርላማ የሰብአዊ መብት ኮሚቴ ሰብሳቢና ከሌሎች የፓርላማ አባሎች ጋር ተወያይተዋል ። ዙማና ባሮሶ ከተነጋገሩ በኋላ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለው የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic