የአፍሪቃና አውሮፓ የቴክኖሎጂ ትብብር | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 17.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የአፍሪቃና አውሮፓ የቴክኖሎጂ ትብብር

ዘንድሮ 50ኛ ዓመቱን በማሰብ ላይ የሚገኘው የነጻ ነጻ የአፍሪቃ መንግሥታት ማኅበር --የአፍሪቃ ኅብረት ፣ እንደ ኤኮኖሚውና ንግዱ ግንኙነት ፣ ከአውሮፓው ኅብረትም ሆነ ከአባል ሃገራቱ ጋር በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ የሚያደርገው ትብብር ምን ይመስላል?

በአውሮፓ ኅብረት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትብብር ፤ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ የፊንላንድ ዩንቨርስቲ የዓለም አቀፍ ልማት ተጓዳኝነት (UniPID) ነው። በዚያው በ UniPID የ አውሮፓው ኅብረትና አፍሪቃ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ትብብር የፕሮጀክት ሥራ መሪ መሊሣ ፕላት ----

«በእርግጥ፣ የአፍሪቃ ኅብረትና የአውሮፓው ኅብረት የሚተባበሩባቸው በዛ ያሉ የምርምር መስኮች አሉ። እንደእውነቱ ከሆነ ሰፋ ያለ ነው። እነዚህ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች ባለፉት ዓመታ እንደታዘብነው ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፤ የውሃ ልማት ፣ የኃይል ምንጭ ፣ ጤና ፣ እነዚህ ነበሩ እንዳየነው ዋና-ዋናዎቹ ትኩረት የተደረገባቸው ዘርፎች።»

በአውሮፓው ኅብረትና በአፍሪቃ ኅብረት መካከል በግብርናው ዘርፍም ትብብር መኖሩን የጠቆሙት በፊንላንድ ዩንቨርስቲ የዓለም አቀፍ ልማት ክፍል፣ የፕሮጀክት ሥራ መሪ ወ/ት መሊሣ ፕላት’ አፍሪቃ ውስጥ ከየትኞቹ አገሮች ወይም ዩንቨርስቲዎች ጋር ትብብር እንደሚደረግ ፣ በተጨባጭ ሁኔታ ስለተዘረጉ ፕሮጀክቶች ሲያብራሩ---

« UNIPID በሚል ምህጻር የታወቀዉ የፊንላንድ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ዓቀፍ ትብብሩን ትኩረት የሚያደርገዉ ዩኒቨርሲቲዎችን በማገዝና በማደፋፈር ነዉ። አባላት የሆኑ አስር ዩኒቨርሲቲዎች አሉ። አባት የሆኑት ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉም የሚገኙት ፊልናድ ዉስጥ ነዉ። እያንዳንዳቸዉም የራሳቸዉ የሆኑ ሌሎች ተባባሪዎች አሏቸዉ። እኛ በበኩላችን ከዉች ዩኒቨርሲዎች ጋ እንዲተባበሩ ነዉ የምንደግፋቸዉ,,,,,በተለይ በምርምር መስኮች! ከእኛ በኩል በቅርቡ የተዘረጋ ፕሮጀክት አለ። በተጨባጭ ሁኔታ ሁለገብ ግንኙነትን፣ትዉዉቅን፣ በፊንላንድ በአፍሪቃ እንዲሁም በላቲን አሜሪካ ተመራማሪዎች በኩል የሚያስተባብር ነዉ። ሴሚናሮች ይካሄዳሉ፤ ትዉዉቅን የሚያጠናክር እንቅስቃሴ አለ፤ ትብብሩን ለመደገፍ ሥርዓት ያለዉ መድረክ ለመፍጠር ሙከራ እናደርጋለን።»

በሳይንስና ስነቴክኒክ እገዛ የአፍሪቃን ልማት ለማፋጠን ከምርምርና ትብብር በመነሳት ምንድነዉ የሚበጅ ይላሉ?

«እንደሚመስለኝ መሠረታዊ በሆነ አሠራር ለሳይንስና ምርምር ላቅ ያለ ግምት ከልማት ጋር የሚቆራኝ ነዉ። በዚህ ረገድ ለእንቅስቃሴዉ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በአንድ አገር ብቻ ሳይሆን ሰፋ ባለ ማኅበራዊ ኑሮ እይታ በአብዛኛዉ የዓለም ክፍል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ትብብር ያሻል። እንደ እኔ እምነት ላቅ ያለ የገንዘብ ድጋፍንም ሆነ የሃብት ምንጭን ለምርምር እና ሳይንስ ማዋሉ የሚበጅ ነዉ።»

አፍሪቃ በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ እመርታ እንዲያሳይ ከምዕራቡ ዓለም በተለይ ከአውሮፓ በኩል በሚቀርበው የቴክኖሎጂ ሽግግር ወይም ዝውውር ምን ይመስላል?

አምና በናይሮቢ፣ የአፍሪቃ የመጀመሪያው የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ እንዲሁም የፈጠራ ውጤቶች ዐቢይ ጉባዔ የተሳተፉትን ፣ በዚህ ረገድ ሂደቶችን በጥሞና የሚከታተሉትን ፣ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በአስዋኔ የቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ፕሮፌሰር ፣ ዶ/ር ማሞ ሙጬ--

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic