1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአፋር የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው ስጋት እና የክልሉ መንግስት የሰጠው ምላሽ

ዓርብ፣ ጥር 2 2017

በአፋር ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ እየተከሰ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከክልሉ ባሻገር ስጋት ደቅኗል። የመሬት መንቀጥቀጡ ያስከተለው ንዝረት እስከ መዲናዋ አዲስ አበባ ድረስ በተደጋጋሚ እየተሰማ ነዋሪዎችን ስጋት ውስጥ መጣሉ ታይቷል። የ አፋር አባቶች መሬት መንቀጥቀጡ ከፈጣሪ የመጣ ስለሆነ ፈጣሪ እንዲመልስልን ዱአ እናደርጋለን ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4ozGW
Äthiopien Vulkanausbruch in der Region Afar
ምስል Seyoum Getu/DW

የአፋር የመሬት መንቀጥቀጥ እና የክልሉ መንግስት ዝግጁነት

በአፋር ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ እየተከሰ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከክልሉ ባሻገር ስጋት ደቅኗል። የመሬት መንቀጥቀጡ ያስከተለው ንዝረት እስከ መዲናዋ አዲስ አበባ ድረስ በተደጋጋሚ እየተሰማ ነዋሪዎችን ስጋት ውስጥ መጣሉ ታይቷል። በሬክተር ስኬል እስከ 5.5 ድረስ የተመዘገበበት የመሬት መንቀጥቀጡ እስካሁን ድረስ የከፋ ሰብአዊ ጉዳት ባያስከትልም በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል።

በኢትዮጵያ የተደጋገመው ርዕደ መሬት እና ስጋቱ

ክስተቱ በመኖሪያ ቤቶች ፋብሪካዎች እና የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን የአፋር ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ አሊ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም ድረስ በተደጋጋሚ መሰማቱ መቀጠሉን የተናገሩት ኃላፊው የክልሉ መንግስት ከፌዴራል የአደጋ መከላከል እና ዝግጅቱነት ኮሚሽን ጋር በመሆን ተፈናቃዮችን የማስፈር እና የመደገፍ ስራዎችን እየሰራ ነው ብለዋል።

ኤርታሌ
ክስተቱ በመኖሪያ ቤቶች ፋብሪካዎች እና የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን የአፋር ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ አሊ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።ምስል Roberto Moiola/robertharding/picture alliance

የመሬት መንቀጥቀጡ እና ሊወሰድ ይገባል የተባለው ቀጣይ ጥንቃቄ

የአፋር አባቶች ስለ የመሬት መንቀጥቀጡ ምን አሉ ?

የመሬት መንቀጥቀጡ ከፈጣሪ የመጣ ስለሆነ ፈጣሪ እንዲመልስልን ዱአ እናደርጋለን ማለታቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ እና የኢትዮ - ጅቡቲ መስመር ኹኔታ

ወደ ፊት የከፋ አደጋ ቢከሰት ዝግጁነቱ ?

በክልሉ በዚህ ልክ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው መሆኑን የገለጹት የኮሙኒኬሽን ኃላፊው ወደ ፊት የከፋ አደጋ ቢከሰት ጉዳት ለመቀነስ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው።

ታምራት ዲንሳ