የአፋር መድረክ ጉባኤ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 31.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአፋር መድረክ ጉባኤ

በአንድነት ለሰላምና እድገት በሚል መርህ በተዘጋጀው በዚሁ ጉባኤ ላይ በቤልጅየምና አካባቢው የሚኖሩ የአፋር ተወላጆች የአውሮፓ ህብረት ባለሥልጣናትና የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል ። ስብሰባው የሥራ እቅዶችንና በማፅደቅና ውሳኔዎችን በማሳለፍ እሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ።

የአፋር የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመብት ተከራካሪ ድርጅቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ በተለይም በአፋር ህዝቦች የፖለቲካና ኤኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ ጥናት ያካሄዱ ምሁራን የተካፈሉበት ጉባኤ ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ ትንናት ተጀምሯል ። በ 2 አመት አንዴ የሚካሄደውን ይህኑኑ ጉባኤ ያዘጋጀው የአፋር መድረክ የተባለው ድርጅት ነው ። በአንድነት ለሰላምና እድገት በሚል መርህ በተዘጋጀው በዚሁ ጉባኤ ላይ በቤልጅየምና አካባቢው የሚኖሩ የአፋር ተወላጆች የአውሮፓ ህብረት ባለሥልጣናትና የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል ። ስብሰባው የሥራ እቅዶችንና በማፅደቅና ውሳኔዎችን በማሳለፍ እሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ። ገበያው ንጉሴ ከብራሰልስ ዝርዝሩን ልኮልናል

ገበያው ንጉሴ ፣

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic