የአፈር ለምነት ጥናት በኢትዮጵያ | ጤና እና አካባቢ | DW | 05.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የአፈር ለምነት ጥናት በኢትዮጵያ

አስር የአፍሪቃ ሃገራት ወደ31 ሚሊየን ሄክታር የተጎሳቆለና የተራቆተ መሬት እስከጎርጎሪዮሳዊዉ 2030ዓ,ም ምርታማ መሆን እንዲችል የመጠበቅ ሥራ ለመሥራት መዘጋጀታቸዉ ከአራት ሳምንታት በፊት ነዉ የተሰማዉ። በዚህ ዘመቻም ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬንያ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳ፣ ማላዊ ኒዠር እና ሌሎች አምስት ሃገራት ተሳታፊ ናቸዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:18
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
11:18 ደቂቃ

የአፈር ለምነት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በዓይነቱ የተለየ የአፈር ለምነት ጥናት ማካሄዷን መረጃዎች ያመለክታሉ። እንዲህ ያለዉ ጥናት በአፍሪቃ ሲካሄድም ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ መሆኗም ተገልጿል።

Konso

እርከን በኮንሶ አካባቢ

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ የዘርፉ ባለሙያ እንደሚሉት ከሆነም ከመላዉ ዓለምም ቢሆን ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ ብዙዎች ይህን ጥናት ለማካሄድ አልደፈሩም። በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡን የዘርፉ ባለሙያ ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ አገራዊ የአፈር ለምነት ዳሰሳ ጥናት መርሃ ግብር ኃላፊ ናቸዉ። ፕሮፌሰሩ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ላለፉት አራት ዓመታት በ495 ወረዳዎች አገራዊ የአፈር ለምነት ዳሰሳ ጥናት አካሂዳለች። በዚህ የዳሰሳ ጥናትም በየአካባቢዉ የሚገኘዉ አፈር የትኛዉ ንጥረ ነገር እንደጎደለዉ ለመገንዘብ ተችሏል። ጥናቱ የሰብል ምርትና ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ እና እያሽቆለቆለ የመጣዉን የአፈር ለምነት ይዞታም ለማሻሻል ያለመ ነዉ። የዳሰሳ ጥናቱ ምን ምንን አካቷል? በምግብ እጥረት ችግር ለሚጎዳዉ ወገንስ የሚያመጣዉ ፋይዳ ምን ይሆን? ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያገኙታል።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic