የአጼ ቴዎድሮስ ቆንዳላ መመለስ ታሪካዊ ነዉ  | ኢትዮጵያ | DW | 26.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

 የአጼ ቴዎድሮስ ቆንዳላ መመለስ ታሪካዊ ነዉ 

ባለፈዉ ሳምንት ብሪታንያ ከዛሬ 150 ዓመት በፊት ከንጉሠ-ነገሥት ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ አስከሬን ላይ ቆርጣ የወሰደችውን የሹሩባ ቁራጭ መመለስዋ ኢትዮጵያዉያን አስደስቶአል፤ ስለ ቅርስ ጉዳይ የሚቆረቆሩ ምሁራንንም እሰየዉ አስኝቶአል። የታሪክ አዋቂዉ አቶ አሉላ ፓንክረስት የአጼ ቴዎድሮስ ቁንዳላ መመለስ ታሪካዊ ነዉ ፤ ሲሊ ነዉ የገለፁት። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:51

«የፀጉሩ መጠንም ሆነ ርዝመት በጣም ትንሽ ነዉ።»

ከዛሬ 150 ዓመት በፊት ከንጉሠ-ነገሥት ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ አስከሬን ላይ ቆርጣ የወሰደችውን የሹሩባ ቁራጭ መመለስዋ ኢትዮጵያዉያን አስደስቶአል፤ ስለ ቅርስ ጉዳይ የሚቆረቆሩ ምሁራንንም እሰየዉ አስኝቶአል። የታሪክ አዋቂዉ አቶ አሉላ ፓንክረስት የአጼ ቴዎድሮስ ቁንዳላ መመለስ ታሪካዊ ነዉ ፤ ሲሊ ነዉ የገለፁት። 
የታሪክ አዋቂዉ አቶ አሉላ ፓንክረስት ብሪታንያ ሙዝየም ወደ ሃምሳ ዓመት ግድም የተቀመጠዉ የአፄ ቴዮድሮስ ቁንዳላ ወደ ለንደን ወዳለዉ ቤተ-መዘክር ሊደርስ የቻለዉ ፤ ቴዮድሮስ እጄን ለጠላት አልሰጥም ብለዉ ራሳቸዉን ሰዉተዉ ሲሞቱ የዚያን ጊዜዎቹ የኢንጊሊዝ ወታደሮች ከአፄ ቴዮድሮስ ፀጉር ቆርጠዉ ወስደዉ በግል ካስቀመጡ በኋላ በልጅ ልጆቻቸዉ ወደ ብሪታንያ ሙዚየም የደረሰ መሆኑን መሆኑን ተናግረዋል። ቅርሱን ለመረከብ ወደ ለንደን አቅንተዉ የነበሩት የኢትዮጵያ የባህል የቱሪዝም እና የወጣቶች ሚኒስትር ዶክተር ኂሩት ካሳው ከብሪታንያ ቤተ-መዘክር ጋር የመግባቢያ ሰነድ ፈርመዋል። የመግባቢያ ሰነዱ ብሪታንያ እና ኢትዮጵያ በጥናታዊ ጉዳዮች እና በአቅም ግንባታ ዙሪያ በትብብር ለመሥራት ያስችላቸዋል ነዉ የተባለዉ። የአፄ ቴዮድሮስ ሹሩባ ቁራጭ እስከ ቅርብ ጊዜ በብሪታንያ  ሙዚየም ለሕዝብ እይታ ክፍት እንደነበር በድረ-ገጽም ይታይ እንደነበር እና በኢትዮጵያ በኩል ግፊት ተደርጎ ለእይታ እንዳይቀርብ የታሪክ አዋቂዉ አቶ አሉላ ፓንክረስት መታደጉን አስታዉሰዋል። የብሪታንያ ሙዚየም ለዘመናት የያዘዉን የአጼ ቴዮድሮስ ፀጉርን መመለሱ ወደፊትም ሌሎች ቅርሶችን ለመረከብ መንገድ ከፋች መሆኑን ብሪታንያ የሚገኙት የኢትዮጵያ የባህል የቱሪዝም እና የወጣቶች ሚንሥትር የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ አባተ  ተናግረዋል። ይህ የታሪክ ምሁሩ የአቶ አሉላ ፓንክረስት እምነትም እንደሆን ተናግረዋል። በቅርቡ የወጡ አንዳንድ ዘገቦች እንዳመለከቱት ከብሪታንያ የተመለሰዉ የአፄ ቴዮድሮስ ፀጉር እጅግ ትንሽና የአምስ ሳንቲም ስፋት ማለት ርዝመት ያለዉ ነዉ ይላል ይህ ምን ያህል እዉነት ይሆን? ሙሉ ጥንቅሩን የድምፅ ማድመቻ ማዕቀፉን በመቻን ይከታተሉ። 

 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሠ 

Audios and videos on the topic