የአጼ ቴዎድሮስ ሹሩባ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ ነው  | ኢትዮጵያ | DW | 04.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአጼ ቴዎድሮስ ሹሩባ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ ነው 

የብሪታንያው ብሔራዊ ጦር ቤተ-መዘክር ከ150 ዓመታት በላይ ከሀገር ርቆ የቆየውን የአጼ ቴዎድሮስ ሹሩባ ለመመለስ ጫፍ ላይ መድረሱን ዛሬ ከለንደን ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ የባህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጨምሮ በርካታ ለሀገር ተቆርቋሪ አትዮጵያውያን በብሪታንያ የተዘረፉ ቅርሶች እንዲመለሱ ሲሟገቱ ቆይተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:31

ከመቅደላ የተመዘበሩ ቅርሶች ይመለሳሉ

የብሪታንያው ብሔራዊ ጦር ቤተ-መዘክር ከ150 ዓመታት በላይ ከሀገር ርቆ የቆየውን የአጼ ቴዎድሮስ ሹሩባ ለመመለስ ጫፍ ላይ መድረሱን ዛሬ ከለንደን ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ የባህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር እንዲሁም ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጨምሮ በርካታ ለሀገር ተቆርቋሪ አትዮጵያውያን በብሪታንያ የተዘረፉ ቅርሶች እንዲመለሱ ሲሟገቱ ቆይተዋል። የአጼ ቴዎድሮስ ሹሩባዎች ወደ ብሪታንያ የተወሰዱት ራሳቸውን ካጠፉ በኋላ ምስላቸውን በሳለ ብሪታንያዊ እንደኾነ ይነገራል። በወቅቱ የመቅደላ ጦርነት ብሪታንያ 13 ሺህ ወታደሮቿን ያዘመተች ሲኾን፤ ወታደሮቹ በርካታ የሀገሪቱ ቅርሶችን መዝብረዋል። የባህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር ዶር ኂሩት ካሳውን ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ አነጋግረናቸዋል። የአጼ ቴዎድሮስ ሹሩባዎችን ለመውሰድ ባለፈው ሳምንት ዝግጅት እንደነበር ተናግረዋል። 

የዛሬ 151 ዓመት ብሪታንያ በአጼ ቴዎድሮስ የታሠሩ አውሮጳውያንን ለማስለቀቅ ዘመቻ ባደረገችበት ወቅት ወታደሮቿ በ200 በቅሎዎች እና በ15 ዝኆች ከመቅደላ የኢትዮፕያን ሐብት መዝብረዋል። የንጉሠ-ነገሥቱ ልጅ ልዑል ዓለማየሁም ብሪታንያ ተወስዶ በ18 ዓመቱ አርፎ ተቀብሯል። የልዑሉን አጽም እና የኢትዮጵያ ቅርሶችን ለማስመለስ ጥረት ከተጀመረ ቆይቷል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ተስፋለም ወልደየስ
 

Audios and videos on the topic