የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በማንቸስተር | ዓለም | DW | 23.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በማንቸስተር

በብሪታንያ የማንቸስተር ከተማ በአንድ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ 22 ሰዎች ተገደሉ፣ ወደ 60 የሚጠጉ ደግሞ ቆሰሉ። ከሟቾቹ መካከል ሕፃናትም ይገኙባቸዋል። ጥቃቱ የተጣለው በከተማይቱ አንድ የሙዚቃ ትርዒት በተካሄደበት ቦታ ነው።

የማንቸስተር ፖሊስ እንዳስታወቀው፣ አጥፍቶ ጠፊው ራሱ የሰራውን ቦምብ  ብዙዎች የሙዚቃ ትርዒት ለማየት በተሰበሰቡበት 21,000 ሰው በሚያስተናግደው የ«ማንቸስተር አሬና» አፈንድቷል።  የታዋቂዋ ወጣት ድምፃዊት አርያነ ግራንዴ የሙዚቃ ትርዒት ካበቃ በኋላ ትናንት ሌሊት ከባድ ፍንዳታ መሰማቱን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች አመልክተዋል።  የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ተሪዛ ሜይ ፍንዳታውን « የአሸባሪዎች ጥቃት»  ማለታቸው እና የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ስብሰባ መጥራታቸው ተሰምቷል። በርካታ ፓርቲዎች እጎአ የፊታችን ሰኔ ስምንት ፣ 2017 ለሚካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ የሚያደርጉትን የምርጫ ዘመቻ አቋርጠዋል።  ፍንዳታውን ተከትሎ  የፀጥታ ጥበቃው የተጠናከረ ሲሆን፣ ከመላ ዓለም የሀዘን መግለጫ በመላክም ላይ ነው።

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ 

 

Audios and videos on the topic