የአድዋ የድል በአል በፍራንክፈርት | አፍሪቃ | DW | 12.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የአድዋ የድል በአል በፍራንክፈርት

123ኛው የአድዋ  የድል በዓል በፍራንክፈርት  ከተማ  ባሳለፍነው ቅዳሜ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል። በጀርመን የኢትዮጵያውያን የውይይትና የትብብር መድረክ ባዘጋጀው በዚሁ መርሃግብር መላው ኢትዮጵያውያን በሕብረት በከፈሉት መስዋዕትነት የተገኘው ይህ ድል የኢትዮጵያን ስም ከፍ ያደረገና የዓለምን የታሪክ አቅጣጫ የቀየረ መሆኑ ተገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:41

«የአድዋ ድል ኢትዮጵያውን በሕብረት ያስገኙት ድል ነው»

ይህን የገለፁት የዕለቱ የክብር እንግዳ የአርበኞች ግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአሁኑ ወቅት ግን የሚታየው ዘርን እና ቋንቋን ያማከለ አደረጃጀት በአገሪቱም ሆነ በሕዝቦቿ ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑን ጠቁመዋል።  በዚሁ ሥነ ሥርዓት የተካፈሉት በኢትዮጵያ ኤምባሲ የፍራንክፈርት ቆንጽላ ጽሕፈት ቤት ተወካይ አምባሳደር በረደድ አንሙት በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን የተጀመረውን ለውጥ ለማጠናከር  ተሳትፎአቸውን  አጠንክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።  የዝግጅቱ ታዳሚዎች በኢትዮጵያ የሚታየው የብሔር ግጭት እና የሕዝቦች መፈናቀል አሳሳቢ መሆኑን በመግለጽ መንግሥት ለችግሩ አፋጣኝ እልባት ሊያበጅለት እንደሚገባ በበኩላቸው አሳስበዋል። በዝግጅቱ ላይ የተገኘው እንዳልካቸው ፈቃደ ዘገባ ልኮልናል።

እንዳልካቸው ፈቃደ

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

 

Audios and videos on the topic