የአድማዎች መደጋገም እና ተፅዕኖዎቹ | ኢትዮጵያ | DW | 18.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአድማዎች መደጋገም እና ተፅዕኖዎቹ

ኢትዮጵያ ዉስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሕዝብ የአድማ እንቅስቃሴዎች ተደጋግመዋል። ከቤት ያለ መውጣት፣ የንግድ ቤቶችን ያለመክፈትና መሰል እንቅስቃሴዎች ሕዝቡ ቅሬታዉን ለመንግሥት የሚያደርስበት ስልት ነው የሚሉ አሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:00

የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ተፅዕኖዎች

በሌላ ወገን ደግሞ የአድማ እንቅስቃሴዉ መንስኤ ግልፅ አይደለም፤ እንዲሁም የሀገሪቱ ጠላቶች ያቀነባበሩት ነዉ በሚልም የሚተቹ ወገኖች አሉ። ያም ሆነ ይህ ከዋና ከተማዋ ውጪ በቅርብ ርቀት ሳይቀር የተስተዋሉት እነዚህ አድማዎች በሀገሪቱ ኤኮኖሚ እና ፖለቲካ ላይ ጫና ከማስከተላቸዉ በተጨማሪ የኅብረተሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይም ተፅዕኖዎችን ማምጣታቸዉ ይነገራል። ዶቼ ቬለ ለዚህ ሳምንት የአድማ ጥሪዎች መደጋገም እና ያስከተሉትን ተፅዕኖዎች አስመልክቶ ዉይይት አካሂዷል። ሙሉ ዉይይቱን ከድምፅ ዘገው ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic