የአዴፓ መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 29.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአዴፓ መግለጫ

የአማራ ክልል መሪ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አዴፓ ባለፈው ሳምንት በክልሉ አመራሮች ላይ የደረሰውን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለቻ አወጣ። ድርጅቱ በመግለጫው ምንም እንኳን የድርጅቱ አመራር አካላትን በሞት ቢነጠቅም ኃይሉ እና አንድነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:04

«አንድነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክቷል»

 የድርጊቱ ፈጣሪዎች ያላቸውን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑን የገለጸው አዴፓ፤ መንግሥት እና ድርጅቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ አሉባልታዎችና ያልተጨበጡ መረጃዎች እየተነዙ በመሆኑ ህዝቡ ጉዳዩን እንዲመዝንም አሳስቧል። የአማራ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው አዴፓ ታጋይ መሪዎቹን ቢያጣም ራሱን አጠናክሮ የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ከምንጊዜውም በላይ ጠንክሮ ይሰራል ብሏል፡፡ የመፈንቅለ መንግስቱ ያነጣጣጠረው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ በአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት፣ በፖሊስ ኮሚሽን፣ ብዙሀን መገናኛ ድርጅትንና የግለሰቦችን ቤት ያነጣጠረ እንደነበርም መግለጫው አመልክቷል፡፡ ድርጊቱን የፀጥታ ሓይሉና ህብረተሰቡ ያከሸፈው መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው በዚህም ድርጊቱን ለማክሽፍ የተባበሩትን ሁሉ አመስግኗል፡፡ከባሕር ዳር ወኪላችን ዓለምነው መኮንን አጭር ዘገባ ልኮልናል።

ዓለምነው መኮንን

ዓለምነው መኮንን

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች