የአዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት | ኢትዮጵያ | DW | 01.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት

ከካቢኔ አባላቱ መካከል 21 ዱ አዳዲስ ናቸው ። ከመካከላቸው ሦስት ሴቶች የሚገኙበትን ይህንኑ አዲስ ካቢኔ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀው በሙሉ ድምጽ ነው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:05
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:05 ደቂቃ

በኢትዮጵያ የአዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ  የ30 የካቢኔ አባላትን ሹመት ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው አጸደቁ። ከካቢኔ አባላቱ መካከል 21 ዱ አዳዲስ አባላት ሲሆኑ 9ኙ ደግሞ ነባር አባላት ናቸው ። ከመካከላቸው ሦስት ሴቶች የሚገኙበትን ይህንኑ አዲስ ካቢኔ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀው በሙሉ ድምፅ ነው።  ከዚህ ቀደም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ በክላስተር የማስፈፀም  እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሚባሉ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ መቅረታቸውን  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም አስታውቀዋል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

 

Audios and videos on the topic