የአዳርጋቸዉ ፅጌ ጉዳይ በብሪታንያ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

  የአዳርጋቸዉ ፅጌ ጉዳይ በብሪታንያ

የመብት ተሟጋችቾ እና የምክር ቤት እንደራሴዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ሲያቀርቡ ያሁኑ የመጀመሪያቸዉ አይደለም። የብሪታንያ መንግሥት ግን ለአቤቱታዉ እስካሁን ተገቢዉን ትኩረት አልሰጠም ተብሎ ይወቀሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:32
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:32 ደቂቃ

«ሚንስትሩ አበክረዉ መጣር ይገባቸዋል»

የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸዉን ኢትዮጵያዊ-ብሪታንያዊ ፖለቲከኛ አንዳርጋቸዉ ፅጌን ይፈታ ዘንድ የብሪታንያ መንግሥት ግፊት እንዲያደርግ የመብት ተሟጋቾች እና የብሪታንያ የምክር ቤት እንደራሴዎች ጠየቁ። አምስት የሰብአዊ መብት  ድርጅቶች እና ሰላሳ እንዳራሴዎች ለብሪታንያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ለቦሪስ ጆንሰን በፃፉት ደብዳቤ እንደጠየቁት አንዳርጋቸዉ እንዲፈቱ ሚንስትሩ አበክረዉ መጣር ይገባቸዋል። የመብት ተሟጋችቾ እና የምክር ቤት እንደራሴዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ሲያቀርቡ ያሁኑ የመጀመሪያቸዉ አይደለም። የብሪታንያ መንግሥት ግን ለአቤቱታዉ እስካሁን ተገቢዉን ትኩረት አልሰጠም ተብሎ ይወቀሳል። ሥለ ጉዳዩ የለንደን ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic