የአዲስ አበባ ከተማ እቅድ | ኢትዮጵያ | DW | 05.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአዲስ አበባ ከተማ እቅድ

የኢትዮጵያ መዲናና የአፍሪቃ ሕብረት ማዕከል አዲስ አበባ ከሚያዋስኑ ገጠር ቀመስ አካባቢዎች ጋር የነደፈችው የጋራ ዕድገት መሪ አቅድ ፣ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት፤ ከአንድ ወር ገደማ በፊት፤ በተለይ በመስተዳድር አራት ፣ በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ እንዳሳዩ ፣

በፀጥታ አስከባሪዎች ርምጃ የሰው ሕይወት መጥፋቱ፤ የቆሰሉና ተይዘው የታሠሩም ስለመኖራቸው ተገልጿል። የተማሪዎቹ ተቃውሞ ርምጃው በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የገጠር አርሶ አደሮችን ከርስት ጉልታቸው አፈናቅሎ ለችግር ይዳረጋል የሚል ነበር።

አዲስ አበባ ፣ አሁን ካላት 54 ሺ ሄክታር ስፋት ወደ 1,1 ሚሊዮን ሄክታር ስፋት እንዲኖራት ይደረጋል የሚል ዜና በአንዳንድ የዜና አውታሮች መጠቀሱ ቢታወስም፤ የከተማ ልማት አቅድ አስፈጻሚ አካል ለሀገርና ለውጭ ጋዜጠኞች የሰጠው መግለጫ ፤ አዲስ አበባ ወደላይ እንጂ ወደ ጎን አታድግም የሚል ነው ።

ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic