የአዲስ አበባ አየር ብክለት | ጤና እና አካባቢ | DW | 21.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

የአዲስ አበባ አየር ብክለት

ዓለም ዓቀፍ የጤና ማዕከል የጠቀሰዉ ጥናት የተበከለ አየር የሚይዛቸዉ ከ200 የሚበልጡ ኬሚካሎች የሰዉ ልጅ ቆዳ ያረጀ እንዲመስል እንደሚያደርጉ ያመለክታል። በጥናቱ ዕድሜያቸዉ 30 እስከ 45 የሚሆን ከ200 በላይ የከተማና የገጠር ሴቶች ለናሙና ተወስደዉ፤ ለሚመለከታቸዉ ዕድሜያቸዉ በዕዉነተኛዉ ላይ 10 ዓመት ያህል ከፍ ብሎ እንደሚገምት ተገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:29

አሳሳቢዉ የከተሞች አየር ጥራት

 የኢትዮጵያ የሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ደግሞ የተበከለ አየር ከ180 ሺህ ሰዎች በላይን ለጤና እክል ዳርጓል።  በየዓመቱ በከተማዋ የአየር ጥራት ጉደት ምክንያት 9 ሺህ የለንደን ነዋሪዎች ሕይወት እንደሚያልፍ በቅርቡ የከተማዋ ከንቲባ ለዜና አዉታሮች ገልጸዋል። በዚህ ምክንያትም ወደ ከተማዋ የሚገቡ ቤንዚን እና ናፍታ የሚጠቀሙ ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2006ዓ,ም አንስቶ የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች በየ ዕለቱ ወደ ለንደን ሲገቡ 10 ፓዉንድ ወይም 12,50 የአሜሪካን ዶላር መክፈል ይኖርባቸዋል።  በተሽከርካሪዎች ምክንያት የሚመጣ ብክለትን ለመቀነስ የተለያዩ ሃገራት እንደ አቅማቸዉ መፍትሄ ያሉትን ተግባራዊ ሲደርጉ ይታያል። ለምሳሌ የለንደን ከተማ አስተዳደር ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2003ዓ,ም አንስቶ ወደ ከተማዋ የሚገባ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ 11,50 ፓዉንድ በየዕለቱ እንዲከፍል ወስኗል። ይህም በከተማዋ የሚፈጠረዉን መጨናነቅ ብሎም የአየር ብክለት ለመቀነስ ያለመ ነዉ። የጀርመኗ ፍራይቡርግ ከተማ 500 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የቢስክሌት መንገድ፤ የከተማ ባቡር ሃዲድ ሲኖራት፤ ርካሽና የተሳካለት የሕዝብ መጓጓዣ ሥርዓት አላት። በዚች ከተማ የቤት መኪና ያለዉ በቤቱ አቅራቢያ እንኳን ለማቆም 18 ዮሮ የሚከፍል ሲሆ፤ በተቃራኒዉ መኪና የሌላቸዉን ይበልጥ ለማበረታታት ርካሽ የመኖሪያ ቤት፤ በጣም ብዙ የብስክሌት ማቆሚያ ስፍራ እና በሕዝብ መጓጓዣ በነፃ የመጠቀም ዕድል ያገኛሉ። አምስተርዳም ከመጪዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2025 ጀምሮ በቤንዚን እና በናፍታ የሚሽከረከሩ መኪናዎችን የማገድ ዕቅድ አዉጥታለች። ሙሉ ቅንብሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic