የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ያማረረው የኤሌክትሪክ መቋረጥ | ኢትዮጵያ | DW | 13.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ያማረረው የኤሌክትሪክ መቋረጥ

ነዋሪዎች እንደሚሉት የኤሌክትሪክ መቋረጥ በዕለት ተዕለት ህይወታቸው፤ በንግድ እንዲሁም በምርት ሂደት ላይ አሉታዊ ጫና አሳድሮባቸዋል ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ ችግሩ በማሰራጫና በማከፋፈያ አቅም ውስንነት አንዲሁም በብልሽት ምክንያት መፈጠሩን ለዶቼቬለ አስታውቋል ።

Äthiopien Solarየአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተደጋጋሚና ለረዥም ሰዓታት አንዳንዴም ለቀናት በሚደርሰው የኤሌክትሪክ መቋረጥ መማረራቸውን አስታወቁ ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የኤሌክትሪክ መቋረጥ በዕለት ተዕለት ህይወታቸው፤ በንግድ እንዲሁም በምርት ሂደት ላይ አሉታዊ ጫና አሳድሮባቸዋል ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ ችግሩ በማሰራጫና በማከፋፈያ አቅም ውስንነት አንዲሁም በብልሽት ምክንያት መፈጠሩን ለዶቼቬለ አስታውቋል ። በበዙ ወጪም የማስፋፍትና የማሰራጫዎች የማሻሻል ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር እርእሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic