የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሙከራ ጉዞ | ኢትዮጵያ | DW | 06.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሙከራ ጉዞ

በአሁኑ ሙከራም ለህዝቡ የባቡር አጠቃቀም ትምሕርት እየተሰጠ ነው ። በትራንስፖርት ችግር የተማረሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ባቡሩ ችግራቸውን ያቃልላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል ።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ህዝብን አሳፍሮ የሙከራ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው ። ባቡሩ ከተመረቀ በኋላ አግልግሎቱ የዘገየው ለባቡር ትራንስፖርቱ አስፈላጊ የሆኑ አቅርቦቶች እስኪሟሉ ድረስ እንደነበር የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ለዶቼቬለ ተናግረዋል በአሁኑ ጊዜ ከጥቃቅን ነገሮች በስተቀር ለባቡሩ የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች በሙሉ መሟላታቸውን ሃላፊው አስታውቀዋል ። በአሁኑ ሙከራም ለተጠቃሚው ህዝብ የባቡር አጠቃቀም ትምሕርት እየተሰጠ መሆኑን አስረድተዋል ። ዛሬ በተካሄደ የሙከራ ጉዞ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ያነጋገራቸው በትራንስፖርት ችግር የተማረሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ባቡሩ ችግራቸውን ያቃልላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic