የአዲስ አበባ ማስፋፊያ አቅድና የተማሪዎች ተቃዉሞ | ኢትዮጵያ | DW | 02.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአዲስ አበባ ማስፋፊያ አቅድና የተማሪዎች ተቃዉሞ

ኦሮሚያ መስተዳደር በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ፤ የኦሮሞ ብሔር አባላት የሆኑ ተማሪዎች ፣ የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ፣ ከኦሮሚያ ክልል ቦታ በመጨመር የምትሰፋበትን አካሄድ በሰላማዊ ተቃውሞ ሲገልፁ፤ ከፖሊስ ጋ በተፈጠረዉ ግጭት ቢያንስ 11 መገደላቸውን መንግስትን ጠቅሶ አሶሲየትድ ፕረስ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

በዚህ ሳምንት መግቢያ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን፤ የክልሉ ፖሊስ የተማሪዎቹ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በፀረ መንግስት ኃይሎች ሳይጠለፍ አይቀርም ሲል ባወጣዉ መግለጫ መጥቀሱንም ዘገባዉ አመልክቷል። እንደዘገባዉም ቢያንስ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች የተቃዉሞ ሰልፉ የተካሄደ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ዩኒቨርሲቲዉ ወዳለበት ከተማም ተስፋፍቷል። መንግሥት ፀረ ሰላም ባላቸው በነዚህ ኃይሎች አመፅ 70 ሰዎች መቁሰላቸውም ተገልጿል ። ሆን ተብለው የተነዙ አሳሳች ባላቸው ወሪዎችና ሃሜቶች ግራ የተጋቡ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት የጀመሩት ረብሻ በቁጥጥር ስር መዋሉንም መንግስት ትናንት ማታ ባወጣው መግለጫ

መንግስት አስታውቋል ።ከረብሻው በስተጀርባ አንዳንድ ፀረ ሰላም ያላቸው ኃይሎች እንዳሉበት ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ኣስታውቋል ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ ዋና ፀሃፊ አቶ በቀለ ናዳ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተካሄደው ተቃውሞ ሰላማዊ ቢሆንም በአምቦ ዩኒቨርስቲ ግን ፖሊስ በወሰደው የኃይል እርምጃ የሰው ህይወት ሊጠፋ መቻሉን ገልፀዋል ።ስለተፈጠረዉ ችግር መንስዔና መፍትኄውም የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ ምን ዓይነት ሐሳብ እንዳለው ፣ ተክሌ የኋላ ፤ የፓርቲውንም ሆነ ምክር ቤቱን ዋና ፀሐፊ አቶ በቀለ ናዳን በስልክ አነጋግሯቸዋል።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic