የአዲስ አበባዉ የጀርመን ት/ቤት የመጀመርያ ተመራቂ | የባህል መድረክ | DW | 23.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የባህል መድረክ

የአዲስ አበባዉ የጀርመን ት/ቤት የመጀመርያ ተመራቂ

«ኢትዮጵያዉያኖች ጀርመን ትምህርት ቤት ገብተዉ እንዲማሩ ፈቃድ አልነበረም። እንደማስበዉ መራሔ መንግሥት ሽሮደር ኢትዮጵያ በነበሩበት ጊዜ ይመስለኛል፤ ይህ ችግር አለ በሚል ከኛ ከቀድሞ ተማሪዎች ተጠይቀዉ ይህ ችግር ተፈትዋል። አሁን ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ልጁን እዝያ ማስተማር ይችላል»

የዛሬ 60 ዓመት አዲስ አበባ ከተማ ላይ የጀርመን ትምህርት ቤት በተቋቋመ በሁለተኛ ዓመቱ ከአራተኛ ክፍል ትምህርታቸዉን ጀምረዉ እዝያዉ የሁለተኛ ደረጃ ትምርታቸዉን ካጠናቀቁት የመጀመርያዎቹ ብቸኛ ሁለት ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች መካከል ዶክተር ካሳይ ወልደ ጊዮርጊስ የሰጡን አስተያየት ነበር። በኬሚስትሪ ትምህርት በጀርመን ሃገር የዶክትሪት ማዕረግን ያገኙት አቶ ካሳይ ወልደጊዮርጊስ ዛሬ በኢትዮጵያና በጀርመን ሃገር መካከል ድልድይን ዘርግተዉ የቀድሞዎቹን ተማሪዎች በማገናኘት በሃገራቱ መካከል ያለዉን የቆየ የባህል፣ የእዉቀት ብሎም የኤኮኖሚ ትስስር ይበልጥ እንዲጠነክር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የአዲስ አበባዉ የጀርመን ትምህርት ቤት ከዛሬ ከስድሳ ዓመት በኋላ በምን ደረጃ ላይ ይገኝ ይሆን? በርግጥ በኢትዮጵያ ዉስጥ የጀርመንኛ ቋንቋን የሚናገር ማኅበረሰብ በርከት ብሎስ ይሆን?! የጀርመንን እዉቀት ቀስመዉ ኢትዮጵያዉያ ዉስጥ በማገልገል ላይ ያሉ ዜጎችስ ቁጥር ምን ያህል ይሆን። በለቱ ዝግጅታችን ስድሳ ዓመት የሆነዉን የጀርመን ትምህርት ቤት ይዘን የመጀመርያዉን የትምህርት ቤቱን ተመራቂ በእንግድነት ጋብዘናል።

Audios and videos on the topic