የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ እቅድና ተቃውሞ | ኢትዮጵያ | DW | 13.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ እቅድና ተቃውሞ

የኦሮምያ ክልል መንግሥት እቅዱ በአዲስ አባባ ከተማ አካባቢ ያሉ የኦሮምያ ልዩ ዞን ከተሞችን ለማሳደግ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋትና ከተሞቹንም ዘመናዊ ለማድረግ የታሰበ እቅድ እንጂ የህዝቡን ጥቅሞች አሳልፎ ለመስጠት ያለመ አይደለም ፣ተቃውሞውም የተሳሳተ መረጃን መሠረት ያደረገ ነው ሲል ይከራከራል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 24:49

እቅድና ተቃውሞ


በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኘው የኦሮምያ ልዩ ዞን ጋር ተቀንጅቶ የተዘጋጀው እቅድ ያስነሳው ውዝግብ ዳግም አገርሽቷል ። የተቀናጀው እቅድ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት ሲባል እንደነበረው የኦሮምያን ህዝብና የክልሉንም ጥቅም ያስቀራል መሬትንም ከኦሮምያ ቆርሶ ይሰጣል የሚሉና የመሳሰሉ ተቃውሞዎች እንደገና ተቀስቅሰዋል ። የኦሮምያ ክልል መንግሥት በበኩሉ እቅዱ በአዲስ አባባ ከተማ አካባቢ ያሉ የኦሮምያ ልዩ ዞን ከተሞችን ለማሳደግ በልዩ ዞኑ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋትና ከተሞቹንም ለማዘመን የታሰበ እቅድ እንጂ የህዝቡን ጥቅሞች አሳልፎ ለመስጠት ያለመ አይደለም ተቃውሞውም የተሳሳተ መረጃን መሠረት ያደረገ ነው ሲል ይከራከራል ። መንግሥት ይህን ቢልም በተቀናጀው እቅድ ላይ የተነሳው ተቃውሞ ግን ቀጥሏል ። ከሁለት ሳምንት በፊት እቅዱን በመቃወም በአንዳንድ የኦሮምያ ዩኒቨርስቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተነሳ ተቃውሞ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል ። የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ እቅድና እና ያገረሸው ተቃውሞ በመጪው እሁድ የሚተላለፈው እንወያይ ርዕስ ነው ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic