የ«አዲስ ስታንዳርድ» ህትመት መቋረጥ | ኢትዮጵያ | DW | 25.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የ«አዲስ ስታንዳርድ» ህትመት መቋረጥ

በእንግሊዝኛ እየታተመ አንባብያን እጅ ዘንድ በየወሩ መግባት ከጀመረ አምስት ዓመት የደፈነዉ «አዲስ ስታንደርድ» መጽሔት በኢትዮጵያ ከታወጀዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ምክንያት ከዚህ ወር ጀምሮ እንደማይታተም ባወጣዉ የጽሑፍ መግለጫ አስታወቀ ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:43
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:43 ደቂቃ

የአዲስ ስታንዳርድ ህትመት መቋረጥ

እንደ መግለጫዉ «አዲስ ስታንደርድ» ወርሃዊዉ መጽሔት በማተሚያ ቤት የኅትመት ችግር ከኅትመት ይቋረጥ እንጂ በድረ-ገጽ የሚያስነብበዉን መጣጥፉን አጠናክሮ ይቀጥላል። «አዲስ ስታንደርድ» መጽሔት የተቋረጠበትን ምክንያት በተመለከተ የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ፀዳለ ለማን በስልክ ጠይቀናታል። 
 


አዜብ ታደሰ


ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic