የአዲሱ ፓትሪያርክ ምርጫና አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 01.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአዲሱ ፓትሪያርክ ምርጫና አስተያየት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ትናንት አቡነ ማቲያስ አዲስ ፓትሪያክ አድርጋ መምረጧ ዩናይትድ ስቴትስ ከሚኖሩ የሐይማኖት አባቶችና ምዕመናን ዉግዘትም፥ ድጋፍም፥ ግራ መጋባትም ገጥሟታል


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ትናንት አቡነ ማቲያስ አዲስ ፓትሪያክ አድርጋ መምረጧ ዩናይትድ ስቴትስ ከሚኖሩ የሐይማኖት አባቶችና ምዕመናን ዉግዘትም፥ ድጋፍም፥ ግራ መጋባትም ገጥሟታል።ዩናይትድ ስቴትስ በስደት የሚገኘዉ ሲኖዶስ ምርጫዉንና ተመራጩን ሲያወግዙ፥ አንድ ሌላ የሐይማኖት አባት ደግሞ ምርጫዉ ሕጋዊና ትክክል ብለዉታል።የዋሽግተን ዲሲ ነዋሪ አማኞች ደግሞ በምርጫዉ ሒደትና ቤተ-ክርስቲያን መሪዎች ልዩነት ግራ መጋባታቸዉን ገልፀዋል።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።የፓትሪያርክ ምርጫ።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስኛ ፓትሪያርክ ትናንት አዲስ አበባ ላይ ተመርጠዋል። የ71ዓመቱ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ከሀገር ዉጭ ከ30ዓመታት በላይ መቆየታቸዉን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ከአዲስ አበባ ዘግቧል። የፓትሪያርክ ምርጫዉ የተከናወነዉ የቤተክርስቲያኒቱን አባቶች ሳያግባባ የቆየዉ ልዩነት መፍትሄ ሳያገኝ እንደመሆኑ ከትችት የራቀ አይመስልም። ሆኖም የተመረጡት አባት ማን መረጣቸዉ የሚለዉ የሚታየዉ በሂደት ከሥራቸዉ ነዉ የሚል ተስፋ ያላቸዉ ወገኖች አልጠፉም። ሸዋዬ ለገሠ በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር የሆኑትን መጋቢ ሀዲስ ደጉአለም ካሳን በጉዳዩ ላይ በአጭሩ አነጋግራለች።

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic