1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአደጋ ጊዜ ጥንቃቄ በጀርመን

ሐሙስ፣ ነሐሴ 19 2008

ሰነዱ ሽብር ፈጣሪዎች ድንገተኛ አደጋ ቢጥሉ ጦርነት ቢከፈት ኤሌክትሪክ ቢቋረጥ እንዲሁም የመጠጥ ውሐ ቢመረዝ ምን መደረግ እንዳለበት ይዘረዝራል።

https://p.dw.com/p/1Jplf
Deutschland Vorratslager Notfallration
ምስል picture alliance/Robert Schlesinger

[No title]

የጀርመን መንግሥት ህዝቡን ካልታሰቡ አደጋዎች ለመጠበቅ ፣ ህዝብ እና መንግሥት አብረው መሥራት እንደሚችሉ የሚያሳይ አንድ ሰነድ አውጥቷል ። ሰነዱ ሽብር ፈጣሪዎች ድንገተኛ አደጋ ቢጥሉ ጦርነት ቢከፈት ኤሌክትሪክ ቢቋረጥ እንዲሁም የመጠጥ ውሐ ቢመረዝ ምን መደረግ እንዳለበት የሚዘረዝር ነው ። ሆኖም ለአ ተዘጋጅቶ መጠበቅ አዲስ ባልሆነበት በጀርመን ሽብር ፈጣሪዎች ሊጥሉት ስለሚችሉት አደጋ ፣ አሁን መፍትሄ ለማምጣት መሞከር በህብረተሰቡ ውስጥ ተገቢ ያልሆነ ፍራቻን ማሳደር ነው ሲሉ የሃሳቡ ተቃዋሚዎች ይናገራሉ ። ዝርዝሩን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ልኮልናል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ