የአይ.ኤ.ኢ.ኤ ማረጋገጫ ኢራንና ዩናይትድ ስቴትስ | ዓለም | DW | 18.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአይ.ኤ.ኢ.ኤ ማረጋገጫ ኢራንና ዩናይትድ ስቴትስ

አሜሪካን በደቂቃዎች ውስጥ ነበር በባንኮችና በሌሎችም ዘርፎች በኢራን ላይ የጣለቻቸውን ማዕቀቦች ማንሳቷን ያሳወቀችው ።ሁለቱ ሃገራት የእሥረኞች ልውውጥም አድርገዋል ።

ዓለም ዓቀፉ የአቶም ኃይል ተቆጣጣሪ ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር IAEA ፣ኢራን ባለፈው አመት ከዓለም ኃያላን መንግሥታት ጋር በአወዛጋቢው የኒዪክልየር መርሃ ግብሯ ላይ በደረሰችበት ስምምነት መሠረት ግዴታዎቿን ተወጣለች ሲል ባለፈው ቅዳሜ ማረጋገጫ እንደሰጠ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ኢራን ላይ ጥሎት የቆየውን ማዕቀብ ወዲያውኑ ነበር ያነሳው ። አሜሪካን በደቂቃዎች ውስጥ ነበር በባንኮች በሌሎችም ዘርፎች በኢራን ላይ የጣለቻቸውን ማዕቀቦች ማንሳቷን ያሳወቀችው ።ሁለቱ ሃገራት የእሥረኞች ልውውጥም አድርገዋል ። ይሁንና አሜሪካን አሁንም ከኢራን ጋር በርካታ ልዩነቶች እንዳሏት ፕሬዝዳንቷ ባራክ ኦባማ አስታውቀዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ ልኮልናል ።

በሌላ በኩል አይ.ኤ.ኢ.ኤ ኢራን የተባለችውን ማድረጓን ካረጋገጠ በኋላ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በኢራን ላይ የተጣሉትን ማዕቀቦች ማንሳቱን እሥራኤል ተቃውማለች ። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ ቅዳሜውኑ ባወጡት መግለጫ ኢራን ስምምነቱን ከፈረመች በኋላም የኒዩክልየር ጦር መሣሪያዎች ባለቤት የመሆን ጥረቷን አላቆመችም ሲሉ ከሰዋል ። ከዚህ ቀደም ከኢራን ጋር ሲደረጉ የቆዩትን ድርድሮች በጥብቅ ሲቃወሙ የቆዩት ነታንያሁ ኢራን አሁን ሽብርተኝነትን ማስፋፋት የምትችልበት ተጨማሪ የገንዘብ ምንጭ ይኖራታል ሲሉም ተቃውሞአቸውን ገልፀዋል ። በጉዳዩ ላይ የእስራኤል መንግሥት ስለያዘው አቋም የህዝቡ አስተያየት ምን እንደሚመስል የእየሩሳሌሙን ዘጋቢያችንን ዜናነህ መኮንን በስልክ አነጋግረነዋል ።

ናትናኤል ወልዴ

ዜናነህ መኮንን

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic