የአይቮሪ ኮስት ጠቅላይ ምኒስትር አማዱ ጎን ኩሉባሊ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ጠቅላይ ምኒስትሩ ከአገራቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ስብሰባ ላይ ሳሉ ሕመም ተሰምቷቸው ረቡዕ ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የአይቮሪ ኮስት ጠቅላይ ምኒስትር አማዱ ጎን ኩሉባሊ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።ጠቅላይ ምኒስትሩ ከአገራቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ስብሰባ ላይ ሳሉ ሕመም ተሰምቷቸው ረቡዕ ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ከሁለት ወራት ሕክምና በኋላ ከፈረንሳይ የተመለሱት በቅርቡ ነበር። ጠቅላይ ምኒስትሩ ለመጪው ምርጫ ገዢውን ፓርቲ ወክለው ለፕሬዝዳንትነት ሊወዳደሩ ታጭተው ነበር። ፕሬዝዳንት አላሳን ዋታራን ይተካሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩት የ61 አመቱ ኩሉባሊ ምን ለሞት እንዳበቃቸው የታወቀ ነገር የለም።