የአየር ጠባይ ለዉጥ ማካካሻ | ዓለም | DW | 19.10.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአየር ጠባይ ለዉጥ ማካካሻ

ለአየር ጠባይ ለዉጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል የሚባሉት ባለኢንዱስትሪ አገራት ሊያደርጉት ይገባል የሚባለዉ ማካካሻ እያነጋገረ ነዉ።

default

የ «ኦክሳም» ጠንካራ ደጋፊዎች ፣ለአፍሪቃ ያላቸውን ተቆርቋሪነት፣ በአንድ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ሲያሳዩ፣

የአየር መለወጥ በድሃ ህዝቦች ላይ የሚያስከትለዉን ችግር በተመለከተም በአዉሮጳ ኅብረት ዉይይት ተካሂዷል። ኦክስፋም የተሰኘዉ ግብረሰናይ ድርጅት ከአዉሮጳ የልማት ኮሚሽን ጋ በመተባበር ባዘጋጀዉ በዚህ ዉይይት የአየር ጠባይ ለዉጥ በኑሯቸዉ ላይ ያስከተለዉን ጫና በእማኝነት ለማሳየት ከአዳጊ አገራት የተወከሉ አርሶ አደሮች ተገኝተዉ ምስክርነታቸዉን ሰጥተዋል። ይህን ተፅዕኖ ለመቋቋምም ከአዉሮጳ ኅብረት 35 ቢሊዮን ዩሮ በየዓመቱ እንደሚፈለግ ተጠቁሟል።

ገበያዉ ንጉሤ

ተክሌ የኋላ/ሸዋዬ ለገሠ